Vaseline Petroleum Jelly ጥያቄዎችና መልሶች
Vaseline Petroleum Jelly ምንድን ነው?
Vaseline Petroleum Jelly ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው እ.ኤ.አ. በ 1859 Robert Chesebrough በተባሉ ሰው ነው፡፡ Vaseline Petroleum Jelly 100% የሚሰራው ከንፁህ የፔትሮሊየም ፈሳሽ ሲሆን ይህም ከማዕድን ዘይትና ሰም ውህድ የተሰራ ሆኖ ከ140 ዓመታት በላይ ደረቅ ቆዳን ወደ እንዲያገግምና ጤናማ እንዲሆን የማድረግ ታሪክ አለው፡፡
የ Vaseline Petroleum Jelly ጥቅሞች ምንድን ናቸው?
Vaseline Petroleum Jelly በተጎዳ ወይም በደረቀ ቆዳ ውስጥ እንደ ማገጃ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ ይህ ማገጃ እርጥበትን ሰብስቦ በመያዝ የቆዳዎትን ተፈጥሯዊ የማገገም ሒደት የተፋጠነ በማድረግ ከውስጥ በኩል ቆዳን ወደ ቀድሞው ጤናማ ሁኔታው እንደሚለስ ያደርገዋል፡፡ Vaseline Petroleum Jelly አየርና ውሃን ተቋቁሞ ስራውን የመስራት ባህርይ ያለው ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ ፈሳሽ ያጠረውን ቆዳ፣ የተሰነጠቀ ቆዳ፣ በመጠኑ የተላጠ ቆዳና የተጫረ ቆዳን ከጉዳት ይከላከላል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ቆዳና ከናፍሮችን ከድርቀትና ከመቆርፈድ ይከላከላል፡፡
Vaseline Petroleum Jelly ከሌሎች የፔትሮሊየም ፈሳሽ ምርቶች የተለየ ነውን?
በቀላሉ ለመናገር፣ አዎ ይለያል፡፡ Vaseline Petroleum Jelly ኦሪጂናል የፔትሮሊየም ፈሳሽ ነው፡፡ ከ140 ዓመታት በላይ ቆዳን ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስና እንከን የለሽ ገጽታ ይኖረው ዘንድ ሲያግዝ ቆይቷል፡፡ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ግብዓቶችና የንግድ ምልክት ያላቸውን ሶስት የማጣሪያ ሒደቶችን የምንጠቀም በመሆኑ እያንዳንዱ የምርት መያዣ ዕቃ ንጹህና ወጥ ልስላሴ ያለው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በርካታ ተመሳስለው የተሰሩ ምርቶች ጥራትን በተመለከተ ተመሳሳይ የሆነ ጥብቅ አቋም የላቸውም፡፡ የእኛ Vaseline የሶስትዮሽ ማጣሪያ ከጭንቀት ነጻ የሆነ ግዥ መፈጸምዎን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
Vaseline Jelly የተሰራው ከፔትሮሊየም ከሆነ፣ እኔም ሆነ ልጄ ብንጠቀምበት ለጤና አስተማማኝ ነውን?
አዎ፣ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለስጋት ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ የፔትሮሊየም ፈሳሽ የሚመነጨው ከፔትሮሊየም ነው፣ Vaseline ደግሞ ፈሳሹን በባለሶስትዮሽ የማጣሪያ ሒደት በኩል እንዲያልፍ በማድረግ ደህንነቱን ያረጋግጣል፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ ደግሞ ያልተጣሩ ነገሮችን የሚያስወግድ በመሆኑ ቆዳን የማያስቆጣና አለርጂክ የማይፈጥር ምርትን ያስገኛል፡፡
Vaseline Petroleum Jelly የቆዳዬን ቀዳዳዎች ይደፍናልን?
የለም፣ Vaseline Petroleum Jelly የቆዳ በሽታን የማያስከትል ማለትም የቆዳን ቀዳዳዎች የማይደፍን፣ ቆዳዎትን የማያስቆጣ ወይም የአንገትና የቆዳን በሽታ የማያስከትል ነው፡፡
የ Vaseline ሎሽኖች ከሌሎች ብራንዶች የሚለዩት በምንድን ነው?
የ Vaseline Intensive Care ሎሽኖች ብቻ በቆዳ አለስላሾችና ባለ ሶስትዮሽ የ Vaseline Petroleum Jelly የተጣሩ ጠብታዎችን የያዙ ናቸው፡፡ ይህ በፍጥነት የሚመጥጥና ቅባታም ያልሆነ ውህድ ቆዳ ወደ ውስጥ በመምጠጥ ከውስጥ በኩል ቆዳዎን ወደ ጤናማ ሁኔታው እንዲመለስ ያግዛል፡፡
የቆዳ ድርቀትን የሚስከትሉ ውጫዊ ምክንያቶችን ምን ምን ናቸው?
የቆዳ ድርቀት በአየር ሁኔታ፣ በአካባቢ፣ አንዳንድ ሳሙናዎችና ዲተርጄንቶችን በመጠቀም፣ በአመጋገብ ወይም በማዕከላዊ ማሞቂያ እና ኤር ኮንዲሽኒንግ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ በቆዳዎ ውስጥ የሚፈተሩ ተፈጥሯዊ ዘይቶች በቀን ውስጥ በሚያከናውኗቸው መደበኛ ሥራዎች ምክንያት ሊወጣ ይችላል፣ በዚህም ምክንያት ቆዳዎ የቀድሞ ሁኔታውን ይዞ እንዲቆይ የሚያግዘው ተፈጥሯዊ የልስላሴ መጠበቂያና ያሳጣዋል፡፡ የቆዳዎ የመከላከያ ድንበር እየተዳከመ ሲሄድ ተጨማሪ እርጥበት ከቆዳዎ ውስጥ እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡
በየቀኑ ቆዳዬን ማለስለስ ያለብኝ ለምንድን ነው?
ጤናማ ቆዳ 90% ከውሃ የተሰራ በመሆኑ ቆዳዎ ሰውነትዎን ለመከላከል የሚያስችል ጥንካሬና ቅልጥፍና እንዲኖረው ያስችለዋል፡፡ ቀኑን ሙሉ ሰውነትዎነ አንድ ሊትር ከግማሽ የሚሆን ውሃ ያወጣል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሱት ያሉ ውጫዊ ጉዳዮች ደግሞ ተፈጥሯዊ የእርጥበት መከላከያ ድንበር እንዲፈርስ በማድረግ ውሃ ከሰውነትዎ የሚወጣበትን ሂደት ያባብሰዋል፡፡ የ Vaseline ሎሽኖች አስፈላጊውን እርጥበትና ንጥረ ነገሮች በመተካት ቆዳዎ ወደ ጤናማ ሁኔታው እንዲመለስና በየቀኑ ያማረ እንዲሆን ለማገዝ የሚያስፈልገውን እርጥበት አፍኖ ይይዛል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ