ለፍቅር ቀጠሮ ዝግጁ ለመሆን የሚያግዙ ምከሮች ከዓለም ዙሪያ
ለፍቅር ቀጠሮ ዝግጁ ለመሆን የሚያግዙ ምከሮች ከዓለም ዙሪያ
ለትልቅ የቀጠሮ ፕሮግራም ሲዘጋጁ ደስታና ፍርሃት የተቀላቀለበት ስሜት ይሰማዋል፡፡ ጥፍር ቀለም መቀባት፣ የፀጉርን ውበት መጠበቅና ምርጥ ቀሚስና ተረከዝ ያለው ጫማ መምረጥ፡፡
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሴቶች ለቀጠሮ ምሽታቸው ሲዘጋጁ የነበራቸውን ተሞክሮ በተመለከተ የነገሩንን ሚስጥር እናጋራለን፡፡ እንዴት እንደተዘጋጁ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡
Li Ming, የማርኬቲንግ ኤግዚኪዩቲቭ፣ ሻንጋይ፣ ቻይና፡
“ለእኔ፣ ጉዳዩ ቆዳዬንና ሜክ አፕ የማዘጋጀት ጉዳይ ነው፡፡ ውድ የሆነ የዝግጅት ጊዜ በስሜትና በአካላዊ ሁኔታ ስሜት ውስጥ ሊከትዎ ይችላል፡፡ የሚደሰቱበት ተዓምራዊ ወቅት፡፡ ጊዜዬን የማጠፋበት ክፍል ይኸው ነው፡፡ የአለባበሴን ሁኔታ አስቀድሜ የማዘጋጅ በመሆኑ ምን መልበስ እንዳለብኝ በመጨነቅ ጊዜ አላጠፋም፡፡ ከምንጊዜውም በላይ የማራኪነት ገጽታ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፣ የምንጊዜም ተመራጭ ማስዋቢያቼን መጠቀሙ ደግሞ ተዓምር ይሰራል – በሻወር ውስጥ፣ ፖሊሽ ማድረግ፣ ዘና የሚያደርግ ጠረናማ ማለስለሻና ቢቢ ( የውበት ዘይት) የእኔን አስማት ለመተግበር ዝግጁ ለመሆን ተመራጭ ሽፋን ነው፡፡ ”
Caroline, ጸሐፊ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ዩኤስኤ፡
“ልማዴ ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሻወር የምወስደው ቅጽበታዊ የመነቃቃትና ለፍቅር ዝግጁ የመሆን ስሜት ስለሚፈጥርብኝ ነው፡፡ ከልሳለሳ ቆዳ የበለጠ ተቃራኒ ጾታን የሚስብ ነገር ስለሌለ፣ እግሮቼን በዘይት አሻለሁ፡፡ የምታወቅበትን ሜክ አፕ ማለትም ደማቅ ጥቁር ፈሳሽ ከመጠቀሜ በፊት የምወደውን ሽቶ ሰውነቴ ላይ አርከፈክፋለሁ፡፡ የዓይን ግንኙነትን ቀላል የሚያደርገው በ960ዎቹ የነበረው ሞቃት አየር ነበር፡፡ መታጠፊያ አካባቢ ትኩረት ለመሳብና አድናቆት ለማግኘት የሚያስችሉ አልባሳትን እለብሳለሁ፡፡ በጣም ቀጭን ለመሆን የምጨነቅበት ጊዜ አልፏል፡፡ ወንዶች የሚወዷት ሴት በሰውነቷ የምትተማመነውን እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ፡፡
Robyn፣ ፎቶግራፈር፣ ሲንጋፖር፡
“በእውነቱ ስሜት ውስጥ መሆን አለብኝ፣ አስማታዊና ነጻ የሆኑ ባህርይዎቼን ማውጣት ያለብኝ ሲሆን ይህን ለማድረግ ደግሞ ሙዚቃ ያስፈልገኛል! ለተለያዩ የስሜት ሁኔታዎች የሚስማሙ የተለያዩ ሙዚቃዎች ዝርዝር ስላለኝ፣ በጣም የሚስብ ገጽታዬን ለማጉላት፣ ስሜትን ከፍ የሚያደርግና የሚያነሳሳ ሙዚቃ አዳምጣለሁ፡፡ የውበት አጠባበቅ ሂደቴ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ነው – እንከን የለሽ ቆዳ መኖሩ የግድ ነው፤ ስለሆነም፣ በተለይ እርጥበታማ በሆነ አየር ወቅት ማዕድን ሰራሽ ሜክ አፕ ቆዳዬ እንዲፍታታና ያማረ ገጽታ እንዲኖረው ያስችላል፡፡ ከቆዳ ባሻገር፣ ዓይኔና ከንፈሮቼ ፕሮግራሜን በማሳመር ረገድ ወሳኝ አስተዋጽኦ አድራጊዎች ናቸው፡፡ ቀለል ያለ ግን ያማረ ነገር ሁልጊዜም ጥሩ ነው፡፡ መጠነኛ የዓይን ቀለም መጠቀሙ ምንጊዜም የማራኪነትና ዝግጁነት ስሜት እንዲኖረኝ ያደርጋል፡፡”
Shellie, የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ ለንደን፣ ዩኬ፡
“ልዩ ምሽት ከሆነ፣ አንድ ሰዓት ተኩል የሚሆን ጊዜ ወስጄ የቆዳዬን ውበት ለመጠበቅ እንቀሳቀሳለሁ፡፡ የጥፍር ቀለም ከተቀባሁ በኋላ የማደርገውን ጌጣጌጥ፣ ጫማ ወይም የምይዘውን ቦርሳ ለመምረጥ ብዙ ጊዜ አጠፋለሁ፡፡ ፀጉሬን ለማድረቅና ለማስተካከል የተወሰነ ጊዜ እወስዳለሁ፡፡ የዓይን ሻዳው ተጠቃሚ በመሆኔ ጎላ ያለ የሜክ አፕ ገጽታ በመፍጠር በመጨረሻም ሽቶዬን ረጨት አድርጌ ዝግጅቴን አጠናቅቃለሁ፡፡”
Huong Mai Dao, የትምህርት ዳይሬክተር፣ ሐኖይ፣ ቬትናም፡
“ምንም ዓይነት ነገር ከማድረጌ በፊት፣ ለስላሳና አንጸባራቂ ቆዳ ያለኝ መሆኑን አረጋግጣለሁ፤ ይህም ማለት ጥሩ የሆነ ሰውነትን በሰም የማሸት ሂደት፣ ዘለግ ያለ የገላ መታጠብ ሂደት ወይም ሻወርና የሰውነት ሎሽን መጠቀም ማለት ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጥቃቅን የሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን ፈጽሜ ያማረ ገጽታ ሲኖረኝ የአስደሳችነትና ማራኪነት ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጋል፡፡ የሚያምር ውበቴን በጣም ለማጉላት፣ የሚያማምሩ ዓይኖች፣ አንጸባራቂ ቆዳና ማራኪ ጠረን ያስፈልገኛል፡፡ በዚህ ላይ ለመጨመርና ለታላቅ የቀጠሮ ሰዓት ዝግጁ የመሆን ስሜት እንዲሰማኝ፣ ፀጉሬን እሰራለሁ፣ ቀይ ሊፕስቲክ ተቀብቼ ረዥም ተረከዝ ያለው ጫማ አደርጋለሁ፤ በዚህም የአንዲት ሴት የሚስጥር ቁልፉ ታወቀ ማለት ነው! ”
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ