ጽዳትን የሚመለከት እውነታ
አንዳንድ ጊዜ ውበትን በተመለከተ ምን ማመን እንዳለብን ማወቁ አስቸጋሪ ነው፡፡ በርካታና የተለያዩ አፈታሪኮችና ልማዳዊ አባባሎች አሉ፡፡ ስለሆነም እውነታውን ልንነግርዎና አፈታሪክን ለማስቀረት እንሞክራለን፡፡
አፈ ታሪክ፡ መደበኛ ሳሙና ቆዳን ያደርቃል፡፡
እውነታ፡ መደበኛ ሳሙና ቆዳዎ ድርቀት እንዲሰማው ሊያደርግ ይችላል፡፡ የሰውነት መታጠቢያ ፈሳሽ ወይም ሞራ፣ የእንስሳት ስብ የሌለው ሳሙና ቢጠቀሙ ልዩነቱን ለመረዳት ያስችልዎታል፤ ምክንያቱም እነዚህ ምርቶች ያላቸው የማጽዳትና የማለስለስ አቅም ሞራ ካላቸው ምርቶች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ Dove በውስጡ ሞራ የሌለው ሲሆን የውበት መጠበቂያ ሳሙናዎቻችን የፈጠራ መብታቸው የተጠበቀ የጽዳት ቴክኖሎጂን ያካተቱና ቆዳን ለስላሳና ምቹ የሚያደርግ 1/4ኛ ማለስለሻ ክሬም የያዙ ናቸው፡፡
አፈ ታሪክ፡ ጥሩ የሆነ ገጽታ እንዲኖርዎ በርካታ የተለያዩ የውበት መጠበቂያ ምርቶች ያስፈልጉዎታል፡፡
እውነታ፡ ያነሰ ነገር ከበዛ ነገር ተመራጭ ነው፡፡ የቆዳዎን ልስላሴ ለማስጠበቅ የሚያስፈልግዎ ጥቂት መሰረታዊ ምርቶች ብቻ ናቸው፡፡ አንዳንድ ምርቶች፣ ለምሳሌ Dove® Beauty Bar (ሜክ አፕ የሚያጸዳ፣ የሚያፋፋና የሚያስለቅቅ) የተለያዩ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ከጥቂት ነገር ብዙ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
አፈ ታሪክ፡ ሞራ (የእንስሳት ስብ) ተመራጭ ማጽጃ በመሆኑ በአብዛኞቹ ሳሙናዎች ውስጥ ይገኛል፡፡
እውነታ፡ አብዛኞቹ መደበኛ ሳሙናዎች በውስጣቸው ሞራ መያዛቸው እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ ግብዓቱ ራሱ ለቆዳ እንክብካቤ ጥሩ አይደለም፡፡ ሞራ ለሳሙና መስሪያነት የሚያገለግለው ዋጋው ርካሽና በቀላሉ የሚገኝ ስለሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ሞራ ቆዳን ከመጉዳቱም ሌላ የቆዳ ማሳከክ፣ መቅላትና መቆጣትን ያስከትላል፡፡ ከሻወር ከወጡ በኋላም እንኳን ሰውነትዎ ላይ የተጣበቀ የሳሙና ትራፊን ማስቀረቱ ተለመደ ነው፡፡ Dove በውስጡ ሞራን አልያዘም – ስለዚህም Dove በያዛቸው ምርጥ ግብዓቶች የተነሳ የላከ የቆዳ እንክብካቤ እንደሚሰጥዎ እምነት ሊጥሉበት ይችላሉ፡፡ Dove የፈጠራ መብታቸው የተጠበቀ የጽዳት ቴክኖሎጂን ያካተተና ቆዳን ለስላሳና ምቹ የሚያደርግ 1/4ኛ ማለስለሻ ክሬም በመያዙ ቆዳን ለስላሳና ከሳሙና ጠረን የጸዳ ያደርገዋል፡፡
አፈ ታሪክ፡ ሙቅ ውሃ የቆዳን ቀዳዳ የሚከፍትና ለቆዳዎትም ጥሩ ነው፡፡
አውነታ፡ ትኩስ ሻወር መውሰድ ጥሩ ሃሳብ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የቆዳ ድርቀትን ያስከትላል፡፡ ከዚህ ይልቅ የቆዳዎን ጤንነትና ልስላሴ ለማስጠበቅ ለብ ባለ ውሃና ተስማሚ የሙቀት ሁኔታ ይታጠቡ፡፡ ሙቅ ውሃ የሚያስደስትዎ ከሆነ፣ ወደ ገንዳው ገብተው የሙቀቱን መጠን ከመጨመርዎ በፊት ሻወሩ ለተወሰነ ጊዜ በእንፋሎት እንዲሞላ ያድርጉ፡፡
አፈ ታሪክ፡ ወንዶች ለቆዳቸው የሚያደርጉት እንክብካቤ ከሴቶች ያነሰ ነው፡፡
እውነታ፡ ምንም እንኳን ወንዶች ለአጠቀላይ የቆዳ እንክብካቤያቸው የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ ቢሆንም፣ ያለባቸው አሳሳቢ ሁኔታ ከሴቶች ጋር ተመሳሳይ ፣ አንዳንድ ጊዜም ከሴቶች የበለጠ ነው፡፡ ዕድሜ መጨመር፣ ጉድፍና ደረቅ ቆዳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን የሚያሳስቡ የጋራ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ ወንዶች የፊት ፀጉርን በተመለከተ ለምሳሌም ጺም ሲላጭ የሚፈጠር ቆዳ መቆጣትና በውስጥ በኩል የሚበቅል ጸጉርን የመሳሰሉ ጉዳዮች ያሳስቧቸዋል፤ በዚህም ምክንያት ቆዳቸውን በአግባቡ መንከባከቡ ለእነርሱም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ