ጥሩ ህልም ለማለም
አብልጠው ስለሚወዷቸው ነገሮች ጥሩ ህልም ለማለም የሚቻልበትን መንገድ የማወቅ ፍላጎት አድሮብዎት ያውቃል? የማሪያ ፍራንስ ኤዠያ ወዳጆቻችን ጥሩ ህልም የማለምና የማስታወስ ዕድላችንን ለማስፋት የሚያስችለንን ይህንን መመሪያ አዘጋጅተውልናል፡፡
ጥሩ ህልሞች የማየትን ዕድል ለማስፋት
ከመኝታ በፊት ፕሮቲን መመገብ ይቅርብዎ፡፡ ካርቦሃይድሬት ያላቸው ምግቦች እንቅልፍዎን ያመጣሉ፤ ይህ እውነት ነው፡፡ ለመፈጨት ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ምግቦች (እንደ ፕሮቲንና ስብ ያሉ) የሰውነትዎን የሙቀት መጠን በመጨመር እንቅልፍ ይነሱዎታል፡፡ ሰላም ያለው እንቅልፍ ይወስድዎ ዘንድ የሰውነትዎ ሙቀት መቀነስ አለበት፡፡ ካርቦሃይድሬት ለእንቅልፍ የሚረዳ ሴሮቶኒን የተባለ ኬሚካል እንዲመነጭ በማድረግ ወደህልም አለም የሚያደርጉትን ጉዞ ቀላል ያደርግልዎታል፡፡
እንደራበዎ ወደመኝታዎ አያምሩ፡ ምግብ መብላትዎንና እየራበዎ አለመተኛትዎን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ርሃብ እንቅልፍዎንና ህልምዎን ሊያቋርጥብዎ ይችላል፡፡ ከመኝታ በፊት ትንሽ ሙዝ ወይም አንድ ብርጭቆ ወተት መጠጣት ጥሩ ነው፡፡
ህልም ለማስታወስ
በጠዋት ይነሱ፡፡ ጸሃይ ከመውጣቷ ከ15 ደቂቃ በፊት ይንቁ፡፡ አይንዎን ይጨፍኑና ፀጥ ብለው አእምሮዎ ውስጥ የቀሩ ጥቂት ምስሎች ላይ ያትኩሩ፡፡ በመቀጠል አይንዎን እንደጨፈኑ የተኙበትን አቅጣጫ ይቀይሩ፡፡ ይህን እያደረጉ እያለ በህልምዎ ያዩአቸው ነገሮች አንድ ባንድ ወደአእምሮዎ የመምጣት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ምንም ነገር ወደአእምሮዎ ካልመጣ ግን በህይወትዎ ትልቅ ቦታ ስላላቸው ሰዎች ማሰብ ይጀምሩ፤ የማስታወሱን ሂደት ሊያግዝ ይችላል፡፡
ማስታወሻ ይያዙ፡ ማስታወሻ ደብተርና እስክሪብቶ አልጋዎ አጠገብ በማስቀመጥ እንደነቁ ስላዩት ህልም ማስታወሻ ይያዙ፡፡ አጫጭር ሀረጎችና ስሞች በፍጥነት ስለሚረሱ በቅድሚያ እነሱን ይጻፉ፡፡ ስለአጻጻፍ ዘዬዎ ሳይጨነቁ በእእምሮዎ የመጣልዎትን ነገር በሙሉ በፍጥነት ይጻፉ፡፡የህልም አለም መልዕክት ለማስተላለፍ በቃላት መጫወትን ይወዳል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ