ጤናማ ቆዳ ለመላው ቤተሰብ
ቆዳ ትልቁ የሰውነታችን አካል ሲሆን የሚሸፍነውም አጠቃላይ ሰውነትን ነው፡፡ እንደ ሙቀት፣ ብርሃን እና ኢንፌክሽን ከመሳሰሉ ውጫዊ ኃይሎች ይከላከለናል፡፡ የሰውነታችን የመጀመሪያው የመከላከያ መስመር ሲሆን የሰውነታችንን የሙቀት መጠን የመቆጣጠር፣ የውሃ እጥረትን የመከላከልና ባክቴሪያ ወደ ሰውነት ውስጥ አለመግባቱን የማረጋገጥ ስራን ይሰራል፡፡ ስለሆነም፣ የጥራት ደረጃቸው የተሻሉ የቆዳ እንክብካቤ ምርተችን መጠቀሙ ለቆዳችን ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የጨቅላ ሕጻናት ቆዳ
የጨቅላ ሕጻናት ቆዳ ለስላሳና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል እንደዚሁም ለብዙ ነገሮች ስሱ ነው፡፡ ጠንከር ያሉ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን ከመጠቀም ይልቅ ከሽታና ከቀለም ነጻ የሆኑ የሰውነት ሎሽኖና ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅባቶችን ይጠቀሙ፡፡
እንደ Vaseline petroleum jelly Baby ያለ ባለ ብዙ ተግባር የቆዳ እንክብካቤ ምርት ለስላሳና ምቹ ነው፡፡ በዳይፐር ምክንት የሚፈጠር የቆዳ ሽፍታን ለማከምና የቆዳ መቆጣትን ለመቀነስ ያግዛል፡፡
የታዳጊ ሕጻናት ቆዳ
ጨቅላ ሕጻናትና ልጆች አካላዊ እንቅስቃሴን በጣም የሚያበዙ በመሆናቸው አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚጠፉት በጨዋታና ከቦታ ቦታ በመሯሯጥ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ቆሻሻንና ጀርሞችን ለማስወገድ እጥበት የሚሰፈልግ በመሆኑ የቆዳ እንክብካቤ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የቆዳ እርጥበት እንዲተካ ለማስቻል ሲባል ከእጥበት በኋላ ቆዳ መለስለሱን ያረጋግጡ፡፡ የቆዳን ልስላሴና መፋፋት ለመጠበቅ ለስላሳ የሰውነት ሎሽንን በሳምንት ለጥቂት ጊዜ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ Vaseline dry skin repair በተለይ የተዘጋጁ የግላይሰሪን (እርጥበትን በሁሉም የቆዳ ሽፋኖች ለማዳረስ) እና የ Vaseline® Petroleum Jelly (እርጥበቱን ይዞ ለማስቀረት) ውህዶችን የያዘ ነው፡፡ ደረቅ ቆዳን ለ3ጊዜና ከዚያ በላይ ማገገም እንደሚችል በሕክምና ምርመራ የተረጋገጠለት ነው፡፡
የታዳጊ ወጣቶች ቆዳ
የታዳጊ ወጣቶች ቆዳ ልዩ እንክብካቤ የሚፈልግበት ምክንያት የሆርመን እንቅስቃሴ ጤናማ በነበረ ቆዳ ላይ ችግር ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ነው፡፡ ፊትና አንገት ላይ የሚወጣ የቆዳ በሽታ ብዙውን ጊዜ በታዳጊ ወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን እንደ ጀርባ፣ አንገትና ደረት በመሳሳሉ ሰውነት አካላት ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ የቆዳ በሽታ ቅባታም ስለሆነ ተጨማሪ ልስላሴ አያስፈልገውም የሚል የተሳሳተ እምነት አለ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ቅባታማ ቆዳ የሚያስፈልገውን ልስላሴ ካላገኘ፣ ቅባትን አመንጪ ዕጢዎች ተጨማሪ ቅባት ማመንጨት ይቀጥላሉ!! ቅባትንና ቆሻሻን ለማጽዳት ፊትንና ሰውነትን በየቀኑ ማጠብ ያስፈልጋል፡፡ ፊትን በተገቢው ማለስለሻ ያክሙትና ቅባታማነት ካስቸገረ ደግሞ ከቅባት ነጻ ሆነ ማለስለሻ መተቀምዎን ያረጋግጡ፡፡ እንደ Vaseline aloe soothe ያለ የሰውነት ሎሽን መጠቀም ቆዳን የመመገብና የማገገም ኃይል ያለው ሲሆን በፍጥነት የመምጠጥ ባህርይም አለው፡፡
ዕድሜው የገፋ ሰው ቆዳ
ዕድሜዎ በጨመረ ቁጥር የቆዳዎ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ይሆናል፡፡ ዕድሜው ለጨመረ ቆዳ ተመራጭ ቆዳ እንክብካቤ ምርቶች ድርቀትንና ያልተመጣጠነ የቆዳ ይዞታን የሚያስተካክሉት ናቸው፡፡ ቆዳ የወጣትነትና ጤናማ ገጽታ እንዲኖረው ሲባል ሰውነትን ከታጠቡ በኋላ በየቀኑ ሰውነትን ማለስለስ አስፈላጊ ነው፡፡ Vaseline cocoa glow lotion ቆዳን የሚመግብ ሲሆን እርትበትን ወደ ቆዳ ውስጥ አስርጎ ያስገባል፡፡ ቆዳችን ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን በማድረግ ጤናማና ብርሃናማ ገጽታን ያላብሰዋል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ