የደረቅ ቆዳ ኤስኤኦስ
ደረቅ ቆዳን የሚያስከትሉ በርካታ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ የአየር ሁኔታ አንዱ ምክንያት ነው – እርጥበትን ከቆዳ ስለሚያደርቁ የክረምት ማለዳዎች ወይም ሞቃታማና ወበቃማ ስለሆኑ የበጋ ቀናት ያስቡ፡፡ ነፋሻማ የአየር ሁኔታዎችና ከፍታማ ቦታዎችም የቆዳን ድርቀት ችግር ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ በቤትዎ ውስጥ ያሉ ማሞቂያዎችና ኤር ኮንዲሽነሮች እርጥበትን ከአየር በመሳብ ቆዳዎ ላይ ተጽእኖ ሊሳድር ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በየቀኑ የቤታችንን ጽዳት ለመጠበቅ የምንጠቀማቸው ዕቃዎች አደገኛ ኬሚካሎችን የያዙ ሊሆኑ ስለሚችሉ ከቆዳችን ውስጥ ተፈጥሯዊ እርጥበትን ሊያወጡ ይችላሉ፡፡
ይሁን እንጂ፣ በአዎንታዊ ጎኑ ሲታይ፣ ለደረቅ ቆዳ በጣም ቀላል መፍትሔ አለ፡፡ በቀን ክፍለ ጊዜ ውስጥ ውሃ በመጠጣት የሰውነትዎን ፈሳሽ እንደሚተኩ ሁሉ፣ ቆዳዎንም ማለስለስ ያስፈልግዎታል፡፡ የቆዳን እርጥበት ለመተካት የሚያስችሉ፣ ወደሚያስፈልግበት ቦታ እንደሚለስ የሚያደርጉና ቆዳዎንም ከተጨማሪ ጉዳትና የፈሳሽ ድርቀት የሚከላከሉ የተለያዩ ዓይነት ምርቶች ከ Vaseline የቀረቡ በመሆኑ ቆዳዎ በጣም ከውስጥ እርጥብና በፈሳሽ የተሞላ ይሆናል፡፡
ፈሳሽን መተካት ጤናማና ውብ ቆዳ እንዲኖር አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ነገሮች ዋነኛው ነው፡፡ መደበኛ ክሬሞችና ሎሽኖች በቆዳችን ላይ ለረዥም ጊዜ የማይቆዩ በመሆናቸው በተደጋጋሚ መቀባት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የ Vaseline ሎሽኖች የተለያዩ የቆዳ ላይ እርጥበትን የሚፈጥሩ ሲሆኑ ለቆዳዎ ዓይነት ተስማሚ በሆኑ 3 ዓይነት ምርቶች ቀርበዋል፡ dry skin repair, cocoa glow እና aloe soothe. ቆዳ ጤናማ እንዲሆንና የበለጠ ገጽታና ስሜት እንዲኖረው፣ በቆዳችን ሁሉም ሽፋን ላይ እርጥበትን ይፈልጋል፡፡ የ Vaseline ሎሽኖች በተለይ የተዘጋጁ የግላሰሪን (እርጥበትን በሁሉም የቆዳ ሽፋኖች ለማዳረስ) እና የ Vaseline® Petroleum Jelly ጥቃቅን ጠብታዎች (እርጥበቱን ይዞ ለማስቀረት) ውህዶችን የያዙ ናቸው፡፡
ደረቅ ቆዳ በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል – በተለይም ለድርቀት የተጋለጡት ቦታዎች እጃችን፣ ክርናችን፣ ጉልበታችንና ተረከዛችን ናቸው፡፡ ድርቀት ያለበትን የሰውነትዎን ክፍል ለማርጠብ፣ Vaseline petroleum jelly ከቆዳዎ ጋር ተፈጥሯዊና ውጤታማ የሆነ ሥራን የሚሰራ ንጹህ ፈሳሽ ለመፍጠር ባለ ሶስትዮሽ የማጣሪያ ሒደትን የሚያልፍ ታማኝ ምርት ነው፡፡ Vaseline petroleum jelly ስንጥቅ ተረከዞችን፣ ደረቅ ጉልበትን፣ ሻካራ ክርን እና ደረቅና የደደረ እጅን እንዲገግሙ ያደርጋል፡፡ ውጤቱም ለስላሳና ጤናማነቱ በግልጽ የሚታይ ቆዳ ነው፡፡
ቆዳዎን በየቀኑ ከድርቀት ይከላከሉ፡፡ ጤናማና ውብ መሆን ብቻ ሳይሆን እርስዎም ውብ የመሆን ስሜት ይሰማዎታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ