የውበት አጠባበቅ ጥቆማዎች እና ምስጢሮች
ከየዕለት የውበት አጠባበቅ ተግባሮቻችን የላቀ ጥቅም ለማግኘት ሁልጊዜም አዳዲስ የውበት አጠባበቅ መረጃዎች እና ምስጢሮችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እጅግ አምረው እንዲታዩ የሚያደርጉዎትን 5 ጠቃሚ ተግባራት እነሆ፡፡
ቀላል እና ሁል ቀን ውብ ሆነው መታየት የሚችሉበት ምስጢር፡
- ይህ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከመተኛትዎ በፊት መጠቀምን ያስታውሱዎት ዘንድ አስፈላጊ የቆዳ ውበት መጠበቂያ ምርቶችን ከአልጋዎ ጎን ያስቀምጡ፡፡ በውስጡ የደረቀ ቆዳዎን የሚታደግ ንፁህ የካካዋ ቅቤ ያለውን Vaseline Cocoa Glow lotion ሁል ጊዜ ምሽት ላይ ይጠቀሙት፡፡ ተኝተው ሳሉ ቆዳዎ የሚፈልገውን ርጥበት ያገኛል፡፡
- አይንዎ ጠዋት ጠዋት ያብጣል? በውድ ዋጋ የሚገዙ የዓይን ክሬሞችን ይርሷቸው፡፡ በክያር (cucumber) ቁራጭ አይንዎን ቢያሹት ዕብጠቱ ወዲያው ይጎላል፡፡ የጥሬ ድንች ቁራጮች በአይኖችዎ ላይ ማስቀመጥም ሌላው ዓይን ንቁ ሆኖ እንዲታይ ማድረጊያ መንገድ ነው፡፡
- ለዓይን ማስዋቢያ የተጠቀሟቸውን መዋቢያዎች እንዴት ዓይኖችዎ ላይ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ማድረግ ይቻላል? ከዓይንዎ መልክ ጋር አብሮ የሚሄድ ቀለም ይምረጡ፡፡ ለምሳሌ ለሰማያዊ አይኖች ቡናማ ቀለም፣ ለቡናማ አይኖች ወይነጠጅ ቀለም ተስማሚ ናቸው፡፡ በትክክል የተዛመደ የቀለማት ስብጥር ዓይኖችዎን ውብ አድርጎ ያጎላል፡፡
- ሁል ጊዜ በቦርሳዎ ቁራጭ ጥጥ ይያዙ፡፡ በትክክል ያልተቀመጡ የሊፕስቲክ ምልክቶችን ለማንሳት፣ የአይን ኩልን ለማስተካከል እና አብረቅራቂ የሽፋሽፍት ማስዋቢያዎችን ለማስተካከል (ሰውነት ላይ የሚያብለጨልጩ የመዋቢያ ብሩሽ ቅሪቶችን ከቆዳ ላይ ለማንሳት) ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
- የመዋቢያ ብሩሾችን በማጠብ ስብርባሪዎችን አስወግደው የቆዳዎን ጤንነት ይጠብቁ፡፡ የመዋቢያ ብሩሾችን የሚጠቀሙ ከሆነ በየሳምንቱ ማፅዳትዎን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ያለበለዚያ ባክቴሪያ ሊፈጠርባቸው እና በፊትዎ ዙሪያ ጀርሞችን ሊያሰራጩ ይችላሉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ