የአስደሳች የውበት ሚስጥሮች
የአዲስነት ስሜት እንዲሰማዎና፣ ከሚታየው በላይ በጣም ቀላል የሆነውን ያለ ብዙ ድካም የሚገኝ ውበትን እንዲላበሱ የውስጥ መረጃ እየሰጠንዎ ነው፡፡ ሚስጥሮቻችንን ተደስተው ከጓደኞችዎ ጋር ይካፈሏቸው፡፡
ጭጋጋማ ዓይን
የጭጋጋማ ዓይን ከባድ የሞቃት አየር ያለበትና ዓይንን የሚያጎላ ገጽታ ይፈጥራል፡፡ 2 እጅ የዓይን ቀለም ከፈሳሽ ቀለም ወይም ከእርሳስ ጋር የዓይን ቆብዎ የላይኛው ክፍል ላይና የታችኛው የሽፋሽፍትዎ መስመር ላይ ይጠቀሙ፡፡ ቀጠን ያለ የ Vaseline Petroleum Jelly የዓይን ቆብዎ ላይ ተጠቅመው ዓይንዎን ይጨፍኑና በደንብ ጭምቅ ያድርጉት፡፡ ግፊቱ ሜክ አፑን በተመጣጠነ መንገድ እንዲሰራጭ ያደርገዋል፡፡ ማንኛውንም የተንጠባጠበ ሜክ አፕ በማጽዳት ጠቆር ያለ የቅንድብ መቀንደቢያ ተጠቅመው ውብ ገጽታን ይላበሱ፡፡
የሚስማማዎ ትክክለኛ ቀለም
አዲስ የሊፕስቲክ ሼድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚጠቀሙበት ወቅት፣ የጣትዎ ጫፍ ላይ የሚገኘው ፓድ ላይ መጠነኛ ቀለም ይጠቀሙ፡፡ በጥፍርዎ ጫፍ ላይ የሚገኘው ቆዳ ከተፈጥሯዊ የከንፈር ሁኔታዎ ጋር ተቀራራቢ በመሆኑ ቀለሙ ለእርስዎ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ማወቁ ቀላል ይሆናል፡፡ ቀለሙ ለፊትዎ ተስማሚ መሆኑን ለማየትም ጣትዎን ወደ አፍዎ አቅጣጫ መያዝ ይችላሉ፡፡
የተዛነፉ የቅንድብ ፀጉሮችን መቆጣጠር
ንጹህ የጥርስ ብሩሽ ወይም መቀንደቢያ በመጠቀም ቅንድብዎን ያፅዱ፡፡ ቅንድብዎን በማዕዘን አቅጣጫ በማበጠር ከዚያም በፀጉር ተፈጥሯዊ አቅጣጫ መሰረት ወደ ላይ አቅጣጫ ያስተካክሉት፡፡ ቀኑን ሙሉ የቅንድብዎን ፀጉር በቦታው እንዲቆይ ለማድረግ የተወሰነ መጠን ያለው Vaseline Petroleum Jelly ይጠቀሙ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ