የተለያያ የአካባቢ ሁኔታ በቆዳዎ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ
አብዛኞቻችን ፀሐይ በቆዳችን ላይ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ውጤቶች እናውቃለን፤ ነገር ግን ቅዝቃዜ በቆዳችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ የምናውቅ ጥቂቶች ነን፡፡ ቀዝቃዛ አየርና ነፋስ በቆዳችን ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም የተፈጥሮ ዘይት በማሟጠጥ ቆዳችን ቀለሙ ቀይ፣ የሚያሳክክ፣ መጥፎ ምልክት ያለበት እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከቤት ውጭ ጊዜ የሚያሳልፉ ከሆነ መደበኛ በሆነ መንገድ ለቆዳችን በትክክለኛዎቹ ምርቶች ፈሳሽ እንዲያገኝ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለቆዳዎት ፈሳሽ መስጠቱ በተለይ አስፈላጊ የሚሆነው ደግሞ ለአትሌቶችና ተራራ ለሚወጡ፣ ብስክሌት ለሚጋልቡ፣ ለሚሮጡና ለሚዋኙ ሰዎች ነው፡፡ Vaseline cocoa glow በግላይሰሪን የበለጸገ ሲሆን ይህም ቆዳችን እርጥበት እንዲያገኝ በማድረግ ጉዳት አድራሽ የአካባቢ ተጽእኖዎች የሚያስከትሉትን ጫና ለመቋቋም ያስችላል፡፡ ምንጊዜም የፀሐይ መከላከያ መጠቀምዎን አይርሱ -በክረምት ወቅት ቢሆንም እንኳ!
ኤር ኮንዲሽነርና የቤት ውስጥ ማሞቂያም የቆዳን ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፤ ምክንያቱም በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን አየር ስለሚያደርቁት በቆዳ ውስጥ ያለውን እርጥበት እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡ እርጥበትን የሚፈጥር መሳሪያ መጠቀሙ በአየር ውስጥ የባከነውን ማንኛውም እርጥበት በመተካት ችግሩን ለመቀነስ ያስችላል፡፡ በጎድጓዳ ሳህን ውሃ ሞልተው አልጋዎ አጠገብ ወይም የሥራ ቦታ ጠረጴዛዎ ላይ ቢያደርጉት የአየሩን የእርጥበት ይዘት እንዲጨምር ሊያግዝ ይችላል፡፡ የማሞቂያ ወይም ኤር ኮንዲሽነሩን መካከለኛ መጠን ላይ ያድርጉት፤ መጠኑ የበዛ ከሆነ ግን ቆዳዎ ላይ አሉታዊ ውጤትን ያስከትላል፡፡
ውሃ መጠጣትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፣ ይህን ማድረጉ ጤናማና እንከን የለሽ ቆዳ እንኖር ከሚያስፈልጉ በጣም ጠቃሚ ግብዓቶች አንዱ ነው፡፡ እንደ Vaseline aloe soothe ያለ ለዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚውል ሎሽን ምንጊዜም በቦርሳዎ፣ በሥራ ቦታ ጠረጴዛዎ ወይም በቤትዎ አካባቢ እንዲኖር ያድርጉ፡፡ ቆዳዎ ድርቀት ሲሰማው፣ ድርቀት በሚታይባቸው አካባቢዎች ላይ በሙሉ ሎሽኑን ይቀቡት፡፡
በአውሮፕላን ተጉዘው የሚያውቁ ከሆነ፣ በቆዳዎ ላይ የድርቀት ስሜት ሲሰማዎ አስተውለው ሊሆን ይችላል፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለው ሪሳይክል የተደረገ አየር እጅግ በጣም ደረቅ ሆኖ ምንም ዓይነት እርጥበት የሌለው በመሆኑ በቆዳ ላይ ድርቀት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ እነዚህን ድርቀት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ለመቋቋም የተሻለ መንገድ የሚሆነው የአልኮል መጠጥ አለመጠጣት ነው፤ አልኮል መጠጣት የሰውነት ስርዓትን ፈሳሽ በበለጠ ሁኔታ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ሰውነትዎ በቂ የውሃ መጠን ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ከበረራ በፊት፣ በበረራ ወቅትና ከበረራ በኋላ ይጠጡ፡፡ ከንፈሮችዎና የአፈንጫ ቀዳዳዎ እንዳይደርቅ ለመከላከል መጠነኛ Vaseline petroleum jelly Vitamin E ይጠቀሙ፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች ጎን ለጎን፣ የወቅት መለዋወጥና ወደ ከፍታማ ቦታ ጉዞ ማድረግ ቆዳዎን ሊያደርቀው ይችላል፡፡ እርጥበት ከቆዳዎ ሳይወጣ እንዲቀርና ቆዳዎም እንዲያገግም ለማድረግ ተገቢ የሆነውን የ Vaseline ሎሽን ወይም የፔትሮሊየም ፈሳሽ ይጠቀሙ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ