የቫዝሊን የቆዳ እንክብካቤ ጥቆማዎች፡ በስፖርት ሜዳ ላይ ለሰውነትዎ ቆዳ ልዩ ጥበቃ ያድርጉ
ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን ይከተላሉ፤ ጥሩ አማካሪ አለዎት፤ በየሳምንቱ ጂም ይሄዳሉ፤ በቃ እርስዎ ተራራን ለመግፋት የሚያስችል በቂ መነሳሳት አለዎት! ግሩም ነው፤ ነገር ግን ሰውነትዎን ለመጠበቅ የሚያደርጉት የዘወትር አካላዊ እንቅስቃሴ የቆዳዎን ሁኔታ እንዴት ሊቀይር እንደሚችል አስበውት ያውቃሉ? በአስቸጋሪ ስፖርታዊ ጨዋታዎችና አካላዊ እንቅስቃሴዎች አካልዎን ከልክ ያለፈ ሲያሰሩት ቆዳዎም በዚያው መጠን ስራ ይበዛበታል፡፡ ቆዳዎን የሚጠብቁ የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን በመጠቀም ይህን ችግር ሊቀርፉት ይችላሉ፡፡
ወንዶች እንደመሆናችን ብዙ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን እናደርጋለን፡፡ በነዚህ እንቅስቃሴዎች ወቅት ቆዳዎ ሊሰጠው የሚችለውን ምላሽ ወይም ሊያሳየው የሚችለውን ለውጥ በርግጠኝነት ማወቁ ሁልጊዜ የሚቻል ባይሆንም ትክክለኛ የቅባት ምርቶችን በመጠቀም በቆዳዎ ላይ ያለዎትን ቁጥጥር ማጠናከር ይችላሉ፡፡ደረቅ፣ ስስና ቶሎ የሚቆጣ ቆዳ ቆዳ ይልቅ በቀላሉ የመጎዳት ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ቆዳዎን ከአሁኑ ካልተንከባከቡት ከጉዳቱ ላያገግምና ዳግም ጤነኛ ላይሆን ይችላል – ስለዚህ ዛሬውኑ እንክብካቤውን ይጀምሩ፡፡ እንደ Vasline MENbody fast Absorbing Lotion ያሉ ቆዳን የሚያርሱ ቅባቶች ቆዳን ርጥበት እንዲኖረው ከማድረግ በተጨማሪ ከጉዳት ይጠብቁታል፡፡ ይህ ምርት ቆዳ ላይ የማብረቅረቅ ባህሪ ሳይኖረው ለደረቅ ቆዳ ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥና የቆዳዎን ሁኔታ ለማሻሻል እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
እንደ Vaseline Cooling Lotion ያሉ ለቆዳ ርጥበት የሚጠቅሙ ምርቶችን በየቀኑ በመጠቀም ቆዳዎ ለስላሳና ቀዝቃዛ እንዲሆን ያድርጉ፡፡ የደምዎን ዑደትና ዝውውር በመጨመር ቆዳዎን ጠንካራና ለስላሳ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ – ምን ጊዜም ቢሆን ቆዳ ጤናማ እሚሆነው የጉዳቱ መጠን አነስተኛ ሲሆን መሆኑን ያስታውሱ፡፡
የስፖርት ላይ ቁስለቶችና ጉዳቶች በጊዜ ሂደት ቆዳዎ የተዛባ መልክ እንዲኖረው ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በቆዳ ላይ የሚታየው የመልክ ለውጥ እየጎላ በሄደ መጠን በዚያው ልክ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ቆዳዎን ርጥበት እንዲኖረው ሲያደርጉት የተስተካከለ መልክ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህም ቆዳዎን ለመታደግ ሁልጊዜ ሎሽን መጠቀምዎን ያረጋግጡ፡፡
ራሳችንን ጠንካራና ጤናማ አድርገን ብንወስድም ስፖርት ላይ ከሚደርሱብን በርካታ ጉዳቶች አኳያ ካየነው ወንድ ልጅ ቆዳውንና መልኩን ካልተንከባከበው ብዙም አይማርክም፡፡ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ የተጠቀሱትን የቫዝሊን ምርቶችን በመጠቀም ከጠንካራ ስፖርታዊ ውድድር በኋላ በእንቅስቃሴው ሂደት ያጧቸውን ንጥረነገሮች፣ ውሃ እና እርጥበት መተካትዎን አይዘንጉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ