የብብት ቆዳን ጥቁረት ለማስወገድ
ቢለብሷቸው ደስ የሚያሰኙዎትን ልብሶች የማይለብሱበት ምክንያት የብብትዎ ቆዳ ጥቁረት እንዳይታይ ስለፈለጉ ይሆን? ለመሆኑ ስለብብት ቆዳ መጥቆር ምንነት እና ከብዙ ሰዎች በተቃራኒ የርስዎ የብብት ቆዳ የጠቆረበትን ምክንያት ጠይቀው ያውቃሉ?
አላወቁ ይሆናል እንጂ የብብትዎ ቆዳ ተለይቶ ቢጠቁር አንዳች በሽታ ያዘዎ ወይም ህክምና የሚያስፈልገው ችግር አለብዎ ማለት አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ከአንድ ሰው የቆዳ ቀለም ጋር የሚገናኝ ነገር ነው – ቀይ ቆዳ ካላቸው ይልቅ ቆዳችን ጠቆር ያለ ሰዎች በዛ ያለ የቀለም ሰጪ ንጥረነገር ክምችት በውስጣችን ስላለ የብብት ቆዳ ጥቁረት ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ በርግጥም በአጠቃላይ ጥቁር የቆዳ ቀለም ባላቸው፣ በተለይም ደግሞ በሴቶች ላይ የብብት ቆዳ መጥቆር ይከሰታል፡፡ ከሦሥት ሴቶች አንዷ የብብቷ ቆዳ ጥቁር ሲሆን፣ ይህ ማለት ደግሞ የብብት ቆዳ መጥቆር ይሄን ያህል ተጋኖ እንደችግር መታየት ያለበት ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ ይሁንና ይሄን ማለቱ ቀላል ሲሆን፣ በአንፃሩ ሁኔታውን አምኖ መቀበሉ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥናቶች እና ስታቲስቲካዊ ትንታኔያቸው ከሚነግርዎ እውነታ በላይ በራስ መተማመንዎ የበለጠ ያስፈልግዎታል፡፡
ስለዚህ የብብትዎ ቆዳ መጥቆር እንዲኖርዎ የሚፈልጉትን በራስ የመተማመን ስሜት ካሳጣዎ እና ሊለብሷቸው የጓጉላቸውን እጀታ አልባ አልባሳት ከመግዛት እንዲቆጠቡ ካደረገዎ፣ እኛ ልንረዳዎ እንችላለን፡፡ ጥቆር ብብትን ታሪክ አድርገው አዲስ ማንነትዎን ዛሬ ላይ ለመጀመር ከዚህ በታች ያቀረብንልዎን ጥቆማዎች ይከታተሉ፡፡
በምን ምክንያት ተከሰተ፤ እንዴት ላጠፋው እችላለሁ?
- አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ዘወትር በጣም ጠባብ ልብሶችን መልበስ ሊሆን ይችላል፡፡ ገላቸን ከልብስ ጋር ጥብቅብቅ ብሎ ሲገናኝ በመካከላቸው የሚፈጠረው መፈጋፈግ የብብት ቆዳ ጥቁረትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ስለዚህ መፍትሔውን ሳይገምቱ አይቀሩም – በአጭሩ ቆዳዎን ነፃ ያውጡት፤ አየር እንዲያገኝ ክፈተት ይስጡት፤ ሰፋ ያሉ ልብሶችን ይልበሱ፡፡
- የብብት ጥቁረትን ለማስወገድ እየሞከሩ ከሆነ የብብት ፀጉር አወጋገድ ልማድዎን ያጢኑ፡፡ ቶሎ ቶሎ የሚደጋገም የብብት ፀጉርነ የመላጨት ተግባር ቆዳዎን ለጉዳት ይዳርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ለብብትዎ መጥቆር ምክንያት ይሆናል፡፡ መላጫዎን የሚጠቀሙበትን ጊዜም ሆነ ሌሎች የመላጫ መንገድዎችን በመጠቀም የሚተገብሩትን ብብት የመላጨት ተግባር ድግግሞሽ በመቀነስ ሁኔታውን በሚገባ ማሻሻል ይችላሉ፡፡
- በተቆጣ ቆዳ ላይ ተጨማሪ የመቆጣት ችግር የሚያስከትል ዲአዴራንት (ጠረን መለወጫ) መጠቀምም ለብብት ቆዳ መጥቆር አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ የቆዳ መጥቆር ላጋጠመው ብብትዎ ልከኛ እና ለስላሳ፣ እንዲሁም በውስጡ ርጥበት የሚሰጥ ንጥረነገር ያለውየጠረን መለወጫ ዲኦዴራንት መጠቀምዎን ያረጋግጡ፡፡
- የብብት ቆዳ መጥቆር በአመዛኙ ከላይ ከዘረዘርናቸው ምክንያቶች በአንዱ ወይም በሌላው የሚመጣ ቢሆንም ክስተቱ ሌላ ከባድ ችግርን አመልካች ሊሆን የሚችልባቸው ሁኔታዎችም አሉ፡፡ ቆዳው መላላጥ እና መደደር ከታየበት ወይም ብብትዎ ጠቁሮ በሌላ የሰውነት ክፍልዎም ላይ የቆዳ መገጣጠብ ችግር ካጋጠመዎ ሃኪምዎን ያማክሩ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ