የቆዳዎን ዓይነት እንዴት ማወቅ ይችላሉ?
የቆዳዎን ዓይነት ይወቁ
ቆዳዎን በሚንከባከቡበት ወቅት የቆዳዎን ዓይነት ማወቅና መረዳት እንደዚሁም የአኗኗር ዘይቤዎ በቆዳዎ ጤንነት ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚጫዎት ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ በቂ ውሃ መጠጣት፣ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብና በቂ እንቅልፍ ማግኘት የመሳሰሉ መልካም ልማዶች ጤናማ ቆዳ እንዲኖረን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ የቆዳዎን ዓይነት ሲገነዘቡ፣ ትክክለኛውን የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችና የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን በመጠቀም ለቆዳዎ የተሻለ እንክብካቤ ማድረግ ይችላሉ፡፡
በሰውነትዎ ውስጥ ያለው ቆዳ በአጠቃላይ በአራት ዓይነት ይከፈላል፤ እነርሱም፡ ጤናማ፣ ደረቅ፣ ቅባታም እና ስሱ ናቸው፡፡ እነዚህ የቆዳ ዓይነቶች እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ልዩ ባሕርይ ያላቸው ሲሆን ለአንድ የጤና ሁኔታ የሚያስፈልግ የተወሰነ የቆዳ እንክብካቤ ይኖረዋል፡፡ የተለያዩት የቆዳ ዓይነቶች የሚገኙት ዓይን ላይ ብቻ አይደለም፤ ከሰውነትም ጋር ሊገናኙ ይችላሉ፡፡ ተስማሚ ቆዳ እንክብካቤ ምርቶች፣ አመጋገብና የአኗኗር ዘይቤን በመከተል በመላ ሰውነትዎ ላይ ጤናማ ቆዳ እንዲኖርዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ጤናማ ቆዳ
መደበኛ ቆዳ ብዙውን ጊዜ ጤናማና ብሩህ ገጽታ ያለው ሲሆን ቆዳውም የጠራና ከጉድፍ የጸዳ ነው፡፡ ደረቅ ወይም ቅባታም አይደለም፤ ወይም ደግሞ ለምርቶች ወይም ለከፍተኛ የሙቀት መጠን ስሱ አይደለም፡፡
ቅባታም ቆዳ
ቅባታም ቆዳ በቆዳ በሽታና በቆዳ መፈንዳት ችግር የመጋለጥ ዕድል አለው፤ መለያ ምልክቱም አንጸባራቂ ገጽታው ነው፡፡ ቅባታም ቆዳ ከሴቶች ይልቅ በብዙ ወንዶች ላይ የሚከሰት ነው፡፡ በሰውነት ላይ ቅባታም ቆዳ የሚታይበት ክፍል ጀርባና ደረት ላይ ሲሆን በዚህም አካባቢ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የቆዳ መፈንዳት ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡ እንደ Vaselinealoe soothe ያለ የቀላል ክብደት ቆዳ ማለስለሻ ቆዳን እያለሰለሰ የመቅለልና የአዲስነት ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል፡፡
ደረቅ ቆዳ
ደረቅ ቆዳ የሚከሰተው በልስላሴ እጥረት ሲሆን በጣም አልፎ አልፎ ደግሞ በሰውነት ውስጥ ፈሳሽ እጥረት ምክንያት የቆዳ መፈንዳት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ደረቅ ቆዳን መለየት የሚቻለው በፀሐይ በቀላሉ ሲጠቁር እና/ወይም ከጽዳት በኋላ የመጨምደድ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የማሳከክ ስሜት ሲሰማዎ ነው፡፡ ቀጫጨን የፊት ቆዳ መስመሮችን ብዙ ጊዜ በዓይን፣ በአፍ፣ በግንባርና በአገጭ ዙሪያ ማየት የሚቻል ሲሆን የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የፈሳሽ እጥረት ነው፡፡ ደረቅ ሰውነት ቆዳ ብዙውን ጊዜ ማየት የሚቻለው በጉልበት፣ ክርን እና በእጅ ላይ ነው፤ የሚቀረፍ ቆዳን ለመከላከል ተስማሚ የሰውነት ሎሽን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
ስሱ ቆዳ
ስሱ ቆዳ በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊከሰት ሚችል ሲሆን ቆዳ የመድረቅና የመጨማደድ ስሜት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ የቆዳ መቅላት፣ ማሳከክና ማቃጠል ስሜት ያለው ሲሆን ለከፍተኛ የሙቀት መጠን፣ ለፀሐይ መጋለጥና ለአልኮል መጠጥ በጣም ስሱ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕይወቱ የትኛውም ምዕራፍ ላይ ስሱ ቆዳ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሰሱ ቆዳ የፀሐይ ብርሃንን መቋቋም የማይችል ባለመሆኑ አሉታዊና ሕመም የሚያስከትል ውጤትን ለመከላከል ሲባል ለዚሁ ተብለው የተዘጋጁ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን በመጠቀም መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ