የመልካም መዓዛ አስደናቂ ኀይል
አንዳንድ ሰዎች ‘በራስ መተማመን ያለው ሰው ብዙ ደስታ አለው’ በማለት አስተያት ሲሰጡ ይደመጣል፡፡ ደስተኛና ዘና ያለ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ሰው ደግሞ አስደናቂ ነገሮች ከማሳካት የሚያግደው ነገር የለም ሲሉ አስተየታቸውን ያጠናክራሉ፡፡ ነገር ግን ኹሉም ሰው በራስ መተማመን ኖሮት አይወለድም፡፡ ዐይናፋሮች አሉ፡፡ አንዳንዶች ቁጥብ ሌሎች ደግሞ ፈታ ያሉ ናቸው፡፡ አንቺስ ልብሽ እንደሚመኘው በሙሉ ልብ ከሰዎች ጋር ለመቀላቀል በራስሽ ላይ ያለሽ እምነት አንሶሽ ተቸግረሻል? ሐሳብ አይግባሽ፤ በራስ መተማመንን ለማሳደግ የሚረዱ የተለያዩ ጥቆማዎችና ዘዴዎች አሉ፡፡ እናካፍልሻለን፡፡
የሴት ልጅ በራስ መተማመን መነሻው ብዙ ቢኾንም መልካም መዓዛ ዋነኛው ነው፡፡ እያንዳንዱ መዓዛ ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮም ይኹን የተዋሓደ፤ ራስን ከመግለጽ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ መልካም ጠረን ጥሩ ስሜት እንዲኖርሽ ያደርጋል፡፡ መልካም ስሜት ሲኖርሽ ደግሞ በዙሪያሽ ያሉ ኹሉ እንዲያውቁት ትመኛለሽ፡፡ ቀጣዮቹን ከሽቶ ጋር የተያያዙ ጥቆማዎችና ምክሮች ተመልከቺ፤ በራስ መተማመንሽ ከማሳደግ ባለፈ የውስጥ ደስታሽን የሚመጥን መልካም ጠረን እንድትጎናጸፊ ያደርግሻል፡፡
ላንቺ የሚኾነውን ትክክለኛ ሽቶ ለዪ
ትክክለኛውን የሽቶ ዐይነት መለየት የትኛውን የሽቶ ብራንድ መግዛት እንዳለብሽ ለመወሰን ስለሚያስችልሽ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የተለያዩ ሴቶች የተለያየ ፍላጎት ስላላቸው የሚያስደስትሽን እስክታገኚ የተለያዩ ሽቶዎችን እና የሽቶ ብራንዶችን መሞከር ይበጅሻል፡፡ አንዳንዶች የከረሜላ መዓዛ ሲወዱ፤ ሌሎች የዝባድ መዓዛ ይመርጣሉ፡፡ የፋሽን አልባሳትና ቁሳቁስ ምርጫችን ግላዊ እንደኾነው ኹሉ (ይህም ራሳችንን ከመግለጽ ጋር የሚያያዝ) የሽቶ መዓዛ ምርጫችንንም በተመሳሳይ ከግል ምርጫችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡
አሪፍ ጥቆማ፡ የሽቶ መዓዛ ምርጫሽን ከላክስ የገላ ሳሙና ጋር አጣምረሽ ተጠቀሚ፡፡ ገላሽን በላክስ ታጥበሽ ስትወጪ ቆዳሽ መልካም መዓዛ ስለሚጎናጸፍ የምትመርጪውን ሽቶ የበለጠ አጉልቶት በዙሪያሽ ያሉትን ኹሉ እንዲስብ ያደርገዋል፡፡
የልብ ትርታ ቦታዎች ተጠቀሚ
በሰውነታችን ላይ የልብ ትርታችንን በጣታችን በመንካት የምንሰማባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ እነርሱም የእጅ አንጓ፣ ዐንገታችን ላይ እና ከጆሮአችን ሥር ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የደም ሥሮቻችን ለቆዳችን ቅርብ የኾኑባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ልባችን ሲመታ እነዚህን የደም ሥሮች የሸፈነው ቆዳ በመርገብገብ ማራኪ መዓዛ ይለቃል፡፡ በነዚህ ቦታዎች ላይ የመረጥሽውን ሽቶ መዓዛ በትንሹ በመንፋት አካባቢውን በግሩም መዓዛ እንዲያውድ ማድረግ ይቻልሻል፤ አንቺም ከራስ መተማመን በመነጨ ግርማ ሞገስ ጎልተሸ ትታያለሽ፡፡
ማለስለስ አትዘንጊ
የትርታ ቦታዎች ላይ ሽቶ ከመንፋትሽ በፊት ቦታውን በቅባት ማለስለስ አትርሺ፡፡ ምርጫሽ የኾነውን ሎሽን በስሱ በመቀባት በሚገባ አለስልሺ፡፡ በለስላሳ እና ወዛም ቆዳ ላይ የሽቶ መዓዛ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ ከምትወጂውና ከሚያስወድድሽ መልካም መዓዛ ጋር እንድትቆዪ ያደርግሻል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ