የልጅዎን ቆዳ መንከባከብ
አዲስ የተወለደ ሕጻን ያለውን ለስላሳና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል ቆዳ የመሰለ ነገር የለም፡፡ ልጅዎ ግን የራሱን ቆዳ ሊንከባከብ የማይችል በመሆኑ ቆዳው ከመቆጣት፣ ከስሱነትና ከፀሐይ ጉዳት የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ ውጤታማ የቆዳ እንክብካቤ ዘዴዎችን ማወቅዎ ጠቃሚ ነው፡፡
በዳይፐር ምክንያት የሚፈጠር የቆዳ ሽፍታን መከላከልና ማከም
የሕጻናት መቀመጫ በዳይፐር ምክንያት ለሚፈጠር የቆዳ ሽፍታ የተጋለጠ ሲሆን ይህ የሚከሰተው ደግሞ ቆዳ ሲቆጣ ነው – (አብዛኛውን ጊዜ እርጥብና በሚጣበቁ ዳይፐሮች የሚከሰት)፡፡ የልጅዎ ዳይፐር ሲረጥብ ወዲያውኑ ቀይረው የረጠበውን የሰውነት ክፍል በጨርቅ ወይም በፈሳሽ በማጠብ ማንኛውም ሽፍታ ወይም ኢንፌክሽን እንዳኖር ይከላከሉ፡፡ ቆዳውን ለማረጋጋትና ማንኛውም የቆዳን መቆጣት ለመከላከል እንደ Vaseline petroleum jelly ያለ ከሽታ የጸዳ የቆዳ እንክብካቤ ምርት ይተቀሙ፡፡
የሕጻን ልጅ ቆዳን መንከባከብ
ዕድሜያቸው ከስድስት ወር በታች የሆናቸው ሕጻናት ሰውነታቸው በየቀኑ መታጠብ አያስፈልገውም፡፡ ቆዳቸውን በተደጋጋሚ ማጠብ ቆዳውን እንዲደርቅ ሊያደርገው ይችላል፡፡ የመታጠቢያ ጊዜያቸው ቆይታ ከአምስት ወይም ስድስት ደቂቃ እንዳይበልጥ አድርገው ቆዳቸውን በእጅ መዳፍ በመዳበስ ማድረቅ ከመፈተግ ይልቅ ተመራጭ ነው፤ ሰውነታቸውን መፈተጉ ቆዳን ሊያስቆጣ ይችላል፡፡
የገላ መታጠቢያና ሻምፑዎችን የመሳሰሉ አንዳንድ ፈሳሽ ሳሙናዎች ቆዳን ሊያስቆጡ ስለሚችሉ ከሽታማ ሆነ ከቀለም ነጻ የሆኑና ስሱና በቀላሉ ሊጎዳ ለሚችለው የሕጻናት ቆዳ ተስማሚ የሆኑ የሕጻናት እንክብካቤ ምርቶችን መጠቀምዎን ያረጋግጡ፡፡ Vaseline petroleum jelly Baby የልጆችዎ ቆዳ ለስላሳና ከጉዳተ የተጠበቀ እንዲሆን ለማገዝ ሲባል ለልጅዎ ቆዳ በተለይ የተዘጋጀ ምቹና ተስማሚ ቅባት ነው፡፡
ሙቀትም በልጅዎ ቆዳ ላይ በተለይም ላብ የሚያልባቸው ከፍሎች ማለትም አንገት፣ መቀመጫ፣ ብብትና መታጠፊያ ቦታዎች ላይ የቆዳ መቆጣትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል ልጅዎን ላላ ብሎ የሚለበስ ከጥጥ የተሰራ ልብስ ማልበስና አካባቢው ቀዝቀዝ ያለና ደረቅ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
የሕጻን ልጅን ቆዳ ከጉዳት መከላከል
ዕድሜያቸው ከስድስት ወር በታች የሆናቸው ሕጻናት ለቀጥታ የፀሐይ ብርሃን መጋለጥ የለባቸውም ምክንቱም የፀሐይ አልትራ ቫዮሌት ጨረር ስሱ ቆዳቸውን ሊያቃጥለው ይችላል፡፡ የመሸፈኛ ልብስና ሕጻናት ከቤት ውጭ ሲሆኑ ቆዳቸውን ከፀሐይ ጨረር ለመከላከል ተብሎ የተዘጋጀ የሕጻናት እንክብካቤ ምርት ከኤስፒኤፍ (ፀሐይ መከላከያ ግብዓት) መጠቀምዎን ያረጋግጡ፡፡
ተያያዥነት ያላቸው ምርቶች
Original BLUESEAL Petroleum Jelly
Vaseline’s Original BLUESEAL የሚከተለው ባለሶስትዮሽ የማጣሪያ ሒደት በጣም ንጹህ የሆነ ፈሳሽ ቅባት ስለሚፈጥር ከቆዳዎ ጋር በተፈጥሯዊ መንገድ ተስማምቶ ይሰራል፡፡ በውጤቱም ለስላሳና ጤናማነቱ በግልጽ የሚታይ ቆዳ ይኖራል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
Baby BLUESEAL Petroleum Jelly
Vaseline’s baby jelly ለየት ያለና ምቹ ፈሳሽ በመሆኑ ከልጅዎ ቆዳ ጋር ተስማምቶ ስለሚሰራ የልጅዎ ቆዳ ለስላሳና ከጉዳት የተጠበቀ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ