የላክስ ማራኪ መዓዛ ምስጢሮች ፡ የሽቶ አቀባብ አዳዲስ ዘዴዎች
ያለእሱ አይሆንልኝም የሚሉት የሽቶ አይነት አለዎት? ለበርካታ ሴቶች አስበልጠው የሚወዱት ሽቶ ከመልካም መዓዛ ባለፈ ትርጉም አለዉ፡፡ በእርግጥም ክርስቲን ዲኦር በአንድ ወቅት እንዳለችው “የሴት ልጅ የሽቶ መዓዛ ከእጅ ጽህፏ ይበልጥ ስለማንነቷ ይናገራል”፡፡ እኛም ይሄ ትክክል ነው ብለን እናምናለን፡፡
ስለውበት የሚፅፉ ጦማሪዎችና ዘናጭ ሴቶች የሚያዘወትሩትን የሽቶ አጠቃቀም ዘዴ ላክስ ያመላክትዎታል፡፡ እርስዎ ደግሞ ማንነትዎን በተለያዩ መዓዛዎች እንዴት መግለፅ እንደሚችሉ ለመማር ይዘጋጁ፡፡
ስሜትዎን የድምጡ
የሚስማማዎትን ሽቶ ተቀብተዋል ሊባል የሚችለው መዓዛው በተቀቡበት ዕለት የነበረዎትን የስሜት አይነትና ሁኔታ በትክክል ለመግለጽ የሚችል ሲሆን ነዉ፡፡ በቀላሉና በፍጥነት ስሜትዎን ለመግለፅ የሚያስችልዎትን መዓዛ ለማግኘት፣ እንደስሜትዎ አብረው የሚሄዱትን የሽቶ መዓዛዎች በወጉ ያዘጋጇቸው፡፡ ጣፋጭ መዓዛ መላበስዎን ለማስረገጥ ይህ ተመራጩ መንገድ ነው፡፡
በተጨማሪም ሳምንቱን ሙሉ አብልጠው የሚወዱትን ሽቶ (ወይም መለያ መዓዛዎን) ብቻ አይቀቡ፡፡ ይልቁንም አዲስ ነገር በመሞከርና መዓዛዎን በመቀያየር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በዘወትር የመታደስ መንፈስ ይክረሙ፡፡ እስከዛሬ ያልሞከሯቸው አዳዲስ ሽቶዎች ለተለየ ውበትና አዳዲስ ጣፋጭ ጠረኖች መልካም አጋጣሚን ይፈጥራሉ፡፡ በሮዝ አበባ መዓዛና በተለያዩ ቅመሞች የበለፀጉ ሽቶዎች ለዚህ ድንቅ አማራጮች ናቸው፡፡
መንፈስዎን የሚድስልዎትንና በተፈጥሮ ጨዉ ፤ በባሕር ዕጽዋትና በግሩም መኣዛ የበለፀገውን LUX Wake Me Up (በመጠቀም ይነቃቁ፡፡፡፡
የመዓዛ ህብር መፍጠር
ጣፋጭ መዓዛ እንዳለዎት በተለይ ዘወትር ሲነገርዎት እንደመስማት ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ ይህንን አይነት የየዕለት አድናቆት ለመታደል ቀላሉና አስተማማኙ መንገድ የተለያዩ ሽቶዎችን በመጠቀም ማራኪ የመዓዛ ህብርን መፍጠር ነው፡፡
የተላያዩ ሽቶዎች እንዴት ማቀናጀት እንደሚቻል በመማር (ልክ እነደተለያዩ ቀለሞች ውህድ ማለት ነው) በጣም ማራኪ ማዓዛዎችን ማግኘትና ቀኑን ሙሉ ጣፋጭ መዓዛን ተላብሰው መዋል ይችላሉ፡፡ ለዚህ የሚያስፈልጉዎት ትክክለኛ የመዋቢያ ሳሙናዎች፣ ፈሳሽ የሻወር ሳሙናዎች፣ ሎሽኖችና የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶች ናቸው፡፡
ሽቶ መቀባት ይልመዱ
ሽቶ ከተቀቡ በኋላ እጆችዎን ያሻሉ? እንደዚያ ማድረግ የለብዎትም፡፡ ሽቶ በመቀባትዎ ላይ ያለዎትን ርግጠኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው ይህ ተግባር የሽቶውን ምጣኔ ቀይሮ መዓዛው መጥፋት ካለበት ጊዜ አስቀድሞ እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡
ይልቁንም ሽቶውን ከርቀት በመርጨት (እጅዎን አርቀው ከዘረጉበት ርቀት) የሽቶውን መዓዛ በደንብ ይላበሱ፡፡
ሽቶውን በተለያዩ የሰውነትዎ ክፍሎች ላይ በመቀባት የበለጠ ለመግነን ይሞክሩ፡፡ “አንገቴንና ሰዓት የሚያርፍባቸውን የእጆቼን ክፍሎች ሽቶ መቀባት፣ ልብሶቼም ላይ በመጠኑ ነስነስ ማድረግ አዘወትራለሁ” በማለት ልምዷን የምትነግረንን የኒዎርኳን የስፓ አማካሪ የሚራንዳ ብራድሪን ምክር ያድምጡ፡፡ እነዚህን ጥቆማዎች መጠቀም ልዩ ትኩረትን ለመሳብ ይረዳዎታል፡፡
አዳዲስ የሽቶ አቀባብ ዘዴዎች
ዛሬ ዛሬ ለመቀባት የምንችላቸው በጣም ብዙ የሽቶ አማራጮችና የተለያዩ የአቀባብ ዘዴዎች አሉ፡፡ በዚህም የተነሳ አንዳንዴ ለእርስዎ የሚስማማዎትን መዓዛ መምረጥ አዳገች ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት የሚስማማዎትን መዓዛ ለማግኘት ብዙ አማራጮችን መሞከር ይኖርብዎታል፡፡ በመሆኑም ምርጫዎን ቀላል ለማድረግ ይህንን መጠነኛ ጥናት አድርገናል፡፡
ቀኑን ሙሉ ለየት ያለ ጣፋጭ መኣዛ ተጎናፅፈን እንድንውል ሊያደርጉን የሚችሉና የእኛ ምርጫ የሆኑ ሶስት መንገዶችን እነሆ
- ገላዎን ከታጠቡ በኋላ የሚጠቀሟቸው ቆንጆ ሽታ ያላቸው ፓዎደሮች መልካም መዓዛን ለመጎናጸፍ ድንቅ አማራጮች ናቸዉ፡፡
- ገላ የሚታሽባቸውና እምቅና ጠንካራ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች በእጅ ቦርሳ ውስጥ ለመያዝ ቀላል ስለሆኑ ደጋግመው ሊጠቀሟቸው ይችላሉ፡፡
- ሽቶ ያለው ቅባት – በጸጉር መዋቢያ ምርቶች፣ በቆዳ ቀለም ማስተካከያ ምርቶች እንዲሁም ለቆዳ ርጥበት በሚጠቀሟቸው ቅባቶች ላይ ሽቶ በመጨመር ሁልጊዜ ማራኪና አስደናቂ መዓዛን መላበስ ይችላሉ፡፡
የእርስዎስ የሽቶ አጠቃቀም ምን ይመስላል?
አስተያየትዎን እዚህ ጋር በመተው ስለእርስዎ የሽቶ አጠቃቀም ምርጫዎች ይንገሩን፡፡ በነገራችን ላይ በቀጣይ አዲስና ማራኪ መዓዛ ያለው የዉበት መጠበቂያ ምርት ለመግዛት ሲፈልጉ በሽ በሽ የመዓዛ አማራጮች ያሏቸውን የላክስ ምርቶች መሞከር አይዘንጉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ