ዘና የሚያደርግ ሻወርን ለመፍጠር የሚያስችሉ 6 መንገዶች
ጥቂትና ቀላል የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም፣ Dove በየቀኑ የሚወስዱት ሻወር ዘና እንደሚያደርግ የስፓ አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ ስሜት እንዲሰጥዎ ያደርጋል፡፡
1. የሻወር መጋረጃዎን መቀየር
በቀለም ወይም በአሰራሩ የተለየና ቅጽበታዊ የመረጋጋት ስሜት የሚፈጥር አዲስ የሻወር መጋረጃ ይግዙ፡፡ ያሉበትን የስሜት ሁኔታ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ቀላልና ወጪ ቆጣቢ መንገድ ነው፡፡ የተረጋጋና የተፍታታ ሁኔታ ለመፍጠር ደብዛዛና ቀለማቸው የማይጮህ መጋረጃዎች ወይም ስሜት ቀስቃሽ ተሞክሮ ለማግኘት ብሩህና አንጸባራቂ ቀለም ይምረጡ፡፡
2. የተወሰነ ሙዚቃ ያጫውቱ
አንድ የሚመርጡትን ሙዚቃ ማጫወቱ በቀላሉ እንዲፍታቱና እንዲዝናኑ ያግዝዎታል፡፡
3. በዙሪያዎ ማራኪ ጠረን እንዲኖር ያድርጉ
በቀላሉ የሚታወቅና ተፈጥሯዊ መዓዛ ያላቸውንና ለእርስዎ ዘና የሚያደርግና የሚያፍታታ ስሜት የሚፈጥሩ ምርቶች ይጠቀሙ፡፡
4. አካባቢው እንዲሞቅ ያድርጉ
ሙቅና አስደሳች ሁኔታ ለማግኘት ወደ ውስጥ ከመግባትዎ በፊት ሻወሩ እንዲሰራ በማድረግና እንፋሎት በማከማቸት መታጠቢያ ቤቱ እንዲሞቅ ያድርጉ፡፡
5. Dove Beauty Cream Bar በመጠቀም ሳሙና አረፋን ይፍጠሩ
Dove Beauty Cream Bar በመጠቀም ወፈር ያለ የአረፋ ክምችት ይፍጠሩ፡፡ ¼ አለስላሽ ክሬም ስላለው ዘና የሚያደርግ የቆዳ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
6. በእርጋታ ስሜት ውስጥ ሆነው ከራስዎ ጋር በሚያሳልፉት ጊዜ ይደሰቱ
አስደሳቹን ጊዜ በደንብ ለማጣጣም ዓይኖችዎን ጨፍነው በደንብ ይተንፍሱ፡፡ ውበት፣ መታደስ፣ የመፍታታትና ለማንኛውም ነገር ዝግጁ የመሆን ስሜት ይሰማዎታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ