ውበትን ሞቅ ባለ ውኃ!
ከረዥም እና አድካሚ ቀን በኋላ ሰውነት ዘና እንዲል ብሎም ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ሞቅ ባለ ውኃ ገላን መታጠብ ነው፡፡
ደስ ይላል አይደል? ይህንን ማድረጋችን የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጠናል፡፡
ሐሳብን ለመሰብሰብ!
በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ለብቻ መሆን በራሱ ሐሳብን ለመሰብሰብ ያግዛል፡፡ ስለዚህ ሙቅ ውኃ በሰውነትዎ ላይ ሲንሸራተት ያለውን ስሜት እያዳመጡ ለጊዜው ከሚያሳስቡዎት ማናቸውም ነገሮች ውስጥዎን ነጻ ያድርጉ፡፡ ጊዜዎትን በጥበብ በመጠቀም ስሜትዎን ዘና ለማድረግ ይጠቀሙበት፡፡ የውኃውን ፍሰት ተከትለው በአእምሮዎት ውስጥ ለሚተላለፈው የምቾት ስሜት ቦታ ይስጡት፡፡ አእምሮዎን እና ሰውነትዎን ፈታ ለማድረግ የሚረዳዎት ምርጥ መንገድ ነው፡፡
ሰውነትን ዘና ለማድረግ!
በጣም ከባድ ከሆነ ሥራ ወይም ውጥረት ከበዛበት የሥራ ሰዓት በኋላ ሞቅ ባለ ውኃ ውስጥ የተወሰነ ቆይታን ማድረግ ሰውነት ላይ የተፈጠረውን ጫና ረገብ በማድረግ ሰውነት እንዲነቃ ይረዳል፡፡ ለዚህም ብዙ ጠቀሜታዎች ባሉት “ዶቭ” የገላ ሳሙና መታጠብን እንመክራለን፡፡ ምክንያቱም “ዶቭ” ወደ ሁሉም የሰውነትዎ ቆዳ ዘልቆ በመግባት እና ቆሻሻን በማስወገድ የሰውነትዎን ተፈጥሯዊ ልስላሴ እና ውበት ይመልሳል፡፡ ግሩም መዓዛውና ለብ ያለው አስደሳች ውኃ አንድ ላይ ተዳምረው ድካምና ጭንቀትዎን ቀለል ያደርጋሉ፡፡
ቆዳን አንጠጸባራቂ ለማድረግ
“ስቲም” በቆዳ እንክብካቤ እና ውበት ውስጥ ትልቅ ሚና አለው፡፡ “ስቲም” ሲገቡ እና ገላዎን ሲታጠቡ አላስፈላጊ የሞቱ ቆዳዎችን በቀላሉ ከሰውነትዎ ማስወገድና ቆዳዎት ሥር የተሰገሰጉ ቆሻሻዎችን ሙልጭ አድርገው ማጽዳት ይችላሉ፡፡ ይህም ቆዳዎን በሚያንጸባርቅ መልኩ ያጸዳዋል፡፡ እንደ Dove Gentle Exfoliating Beauty Bar የመሳሰሉትን የገላ ሳሙናዎች ከ“ስቲም” ጋር አብሮ መጠቀም ደግሞ የሞቱ የቆዳ ላይ ሴሎችን ከቆዳ ላይ አንሥቶ የውብ እና አንጸባራቂ የሰውነት ቆዳ ባለቤት እንዲሆኑ ያደርግዎታል፡፡
ወደ ሰዉነት ዉሰጥ እርጥበት በቀላሉ እነዲገባ
በሙቅ ውኃ ገላዎትን ከታጠቡ በኋላ ሰውነትዎ ለተጨማሪ ማለስለሻዎች ዝግጁ ይሆናል፡፡ “ስቲም” የተደፈኑ የቆዳ ክፍሎችን በመክፈት የሚጠቀሙት ሰውነት ማለስለሻ በሁሉም የሰውነትዎ ቆዳ ላይኛውና ውስጠኛው ክፍል እንዲዳረስ ያደርጋል፡፡ ከመተኛትዎ በፊት ገላዎትን መታጠብዎት እና በተፈጥሯዊ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ማለስለሻ መጠቀምዎ የሰውነትዎን ቆዳ ልስላሴ እና ውበት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
ስኬታማ ቀንን ለማሳለፍ!
በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ሞቅ ባለ ውኃ እና በDove Beauty Cream Bar ሲታጠቡ ከቆዩ በኋላ በጥሩ እንቅልፍ ይታደሳሉ፡፡ በዚህም ሰውነትዎ ለቀጣዩ ቀን ተግባራቶችዎ ዝግጁ ይሆናል፡፡ በማግስቱ ቆዳዎ ለስላሳ እና አንጸባራቂ፤ የሰውነትዎ መዓዛም ማራኪ ሆኖ ይውላሉ፡፡ አእምሮዎም በአዲስና ውጤታማ ሐሳቦች የተሞላ ይሆናል፡፡. አሁን በሥራ ቦታም ሆነ በቤት ውስጥ ማንኛውንም ነገር በስኬት ለመወጣት ዝግጁ ነዎት፡፡ በምርጡ Dove ሳሙና እና በሙቅ ውኃው ጥምረት ሰውነትዎ በሚገባ ዘና ብሏልና!!
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ