ከእናትዎ የተማሯቸው የውበት ትምህርቶች
አዎ፣ አሁን ስለ ውበት ብዙ ነገር አውቀናል፤ በእርግጠኝነት የተማርነው ደግሞ ምርጥ መምህራን ከሆኑት እናቶቻችን ነው፡፡ የ Dove አድናቂዎቻችን ከእናቶቻቸው ከተማሯቸው ታላላቅ የውበት ትምህርቶች መካል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
“ፈገግታ ምርጥ አጋዥ ኃይል ነው”
ውብና ከልብ የመነጨ ፈገግታ ምንጊዜም ከስርዓት ውጭ አይሆንም፡፡ አዎንታዊነትን ለመግለጽ ምርጥ አማራጭ ሲሆን የደስታ ስሜት በፍጥነት እንዲሰማዎ ለማድረግ ተመራጭ ነው፡፡ እንዲያውም ጤናዎን በማሻሻሉና የወጣትነት ገጽታ እንዲኖርዎ በማድረጉም ይታወቃል፡፡
“ብዙ ሜክ አፕ አትጠቀሚ፣ ራስሽ ውብ ነሽ ”
እናቴ ብዙ ጊዜ ስትናገር ቀለል ያለ ነገር ተመራጭ እንደሆነና እኔም የተሻለ ውበት የሚኖረኝ ብዙ ሜክ አፕ በማልጠቀምበት ወቅት ነው፡፡ የጽዳት አጠባበቅ መመሪያዎትንና የሜክ አፕ አጠቃቀም ጊዜን ማቅለል ውብ የመሆን ስሜት የሚፈጥርብዎን ጽዱ፣ አንጸባራቂና እናትዎ የሚወዱት ገጽታን ያጎናጽፍዎታል፡፡
“ማለስለስ፣ ማለስለስ፣ ማለስለስ!”
ደረቅ፣ ቅባታም፣ ጤናማ ወይም ስሱ ቆዳ ቢኖርዎት፣ ጤናማና ውብ ቆዳ እንዲኖርዎ ማድረግ ከሚችሏቸው በጣም ጠቃሚ ነገሮች መካከል አንዱ ቆዳን ማለስለስ ነው፡፡ ቢያንስ ጠዋትና ማታ በየቀኑ ቆዳ ማለስለሻን ይጠቀሙ፤ ሰውነትዎን ከውስጥ በደንብ ለማራስ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ይጠጡ፡፡
“ቀጥ ብለው ይቁሙ”
እያንደንዷ እናት ጥሩ የሰውነት አቋምን ታበረታታለች፡፡ ቀጥ ብሎ መቆም የጀርባን አጥንት ጤናማ ሲያደርግ በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ራስዎ የመተማመን ስሜት እንዲሰማዎና አክብሮት እንዲያገኙ ያስችልዎታል፡፡
“ውበት የሚመነጨው ከውስጥ ነው”
ውብ ገጽታና ስሜትን መላበስ ጎን ለጎን የሚጓዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ለአንድ ሰው መልካም ነገር ማድረግ ጥሩ ስሜት ይፈጥርብዎታል፤ ደስተኛ ጸባይ ደግሞ ብሩህ ገጽታን ያላብስዎታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ