ከቀዩ ምንጣፍ የዝነኞች ስታይል የሚያነሳሳ መንፈስ
ከቀዩ ምንጣፍ የተወሰነ የስታይል የሚያነሳሳ መንፈስ በመውሰድ ቀጣዩ ምሽትዎ ላይ ድንቅ ውበት ይላበሱ፡፡ Lux እንደ Rihanna፣ Jennifer Lawrence፣ Gwen Stefani እና Jennifer Lopez ያሉ አርቲስቶች ለካሜራ ዝግጁና የቀይ ምንጣፍ ስታይል እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡ ብርሃንና ካሜራ ሲጨመርበት ድንቅ ነው!
Rihanna: ግራሚስ 2014
Rihanna በግራሚስ ቀይ ምንጣፍ ላይ የተራመደችው በጣም የሚያምር ቀይ ልብስ ለብሳ ሲሆን የሁሉንም ትኩረት የሳበ አለባበስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፣ ይህ አለባበስ የ Rihanna’s የተለመደ ሰውነትን የሚያጋልጥ ወይም ስሜት ቀስቃሽ አለባበስ አይደለም፤ ረዥምና አስከ አንገቷ የሚደርስ ሐር ሰራሽ ጋወን ለብሳ ስትታይ አንጸባራቂና ማራኪ ገጽታን ተጎናጽፋ ነበር፡፡
LUX አነሳሽ መንፈስ፡ RiRi’s አስገራሚ ባሕል ጠቀስ የ Azzedine Alaia ቀሚስ ትክክለኛውን የስጋ መጠን የሚያሳይ ነው፤ በመጠኑ ውስጣዊ አካልን የሚያሳይ ቢሆንም፣ ሰውነቷን ስለሸፈነው ዘናጭ እንድትሆን አድርጓት ነበር፡፡ ሴትነትንና ስሜት ቀስቃሽነትን በአንድነት ለማንጸባረቅ ከፈለጉ፣ ትኩረትን ሰቅዞ የሚይዝ ቀይ፣ ደማቅ ቀለምና ስስ ጨርቅ የተሰራ ልብስ ይልበሱ፡፡
Jennifer Lawrence: ኦስካር 2014
Jennifer Lawrence በኦስካርስ ላይ ለብሳ የነበረው ትንፋሽን የሚያሳጣ፣ ባለ ሙሉ ቁመት የ Christian Dior ውጤት የሆነ ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ጋወን ነበር፡፡
LUX አነሳሽ መንፈስ፡ የዝሆን ጥርስና ነጭ ቀለም ዘናጭ የቀለም ምርጫዎች ቢሆኑም፣ Jennifer እስከ ጀርባዋ ድረስ የሚንጠለጠል ከአልማዝ የተሰራ ረዥም የአንገት ሐብል በማሰር ይህንን ዘናጭ ገጽታ ዘመናዊነት እንዲላበስ አድርጋዋለች፡፡ የ Jennifer’s ውብ ገጽታ ለማየት፣ አንድ ነጭ ቀሚስ ከጌጣጌጥ ጋር በማጣመር ፀጉርዎን በተፈጥሯዊ ሜክ አፕ ይሰሩት፡፡
Gwen Stefani: ሜት ቦል 2014
Gwen Stefani የወለል ርዝመት ያለው ባለ አንድ ቀለም ቀሚስ ለብሳ በኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ወደሚገኘው Metropolitan Museum of Art Ball መጥታ ነበር፡፡ ከቀሚሱ ጋር የተጣመረው የምትታወቅበት ቀይ ከንፈሯና ባለ ነጭ ፈዛዛ ቢጫ ፀጉሯና ማዕዘናዊ ግንባሯ ላይ ከሚተኛው ፀጉር ጋር ነው፡፡
LUX አነሳሽ መንፈስ፡ ባለ አንድ ቀለም ጥቁርና ነጭ ምንጊዜም ጊዜ የማይሽረው ቢሆንም፣ Gwen የራሷን ልዩ አስተዋጽኦ ጨምራበት ነበር፡፡ ይህንን ገጽታ ለማሻሻል ጉርድ ቀሚስና ከላይ የሚለበስ ነገር መልበስ፣ እንደዚሁም ትኩረት ሳቢ ቀይ ሊፕስቲክ መቀባት ይችላሉ፡፡
Jennifer Lopez: ጎልደን ግሎብስ 2013
Jennifer Lopez ወደ ጎልደን ግሎብስ ስትሄድ ስሜትን ቀስቃሽ የሆነ አለባበስ ለብሳ ነበር፡፡ አለባበሷ የሰውነትን ህብርና በግልጽ የሚታይ አካልን የሚያንጸባርቅ ነበር፡፡ ባለ ረዥም እጅጌው የ Zuhair Murad ቀሚሷ ጌጣጌጥ ያለበት ኮሌታ ስለነበረው የእጥፋት እንቅስቃሴዎቿ ጋር በሚገባ ተስማምቶ ደስ በሚል ነጭ ስስ ማሰሪያ የታሰረ ነበር፡፡
የ LUX አነሳሽ መንፈስ፡ ማራኪ ማሰሪያና ጨርቆችን በማቀናጀት ትኩረት እርስዎ ላይ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ አጋዥ ክፍሎች ቀለል እንዲሉ በማድረግ ቀሚሱ ሾውን እንዲቆጣጠር ያድርጉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ