አራት ቀላል ተግባራትን በቅደም ተከተል በመተግበር የቆዳ ድርቀትን ይከላከሉ
የቆዳ ድርቀት የሚከሰተው አየር ከቆዳ በሚስበው ርጥበት አማካይነት የቆዳ ሴሎች ስለሚታፈኑና የቆዳዎን ደህንነት የሚጠብቅልዎ ግድግዳ ስለሚዳከም መሆኑን ያውቁ ኖሯል?
በደረቃማ ወቅት ቆዳዎ ልክ እንደወቅቱ የአየር ሁኔታ ሊደርቅብዎት እና ጥሩ ስሜት እንዳይኖርዎ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ አመቱን ሙሉ አምረውና ጥሩ ስሜት እየተሰማዎ እንዲከርሙ እንፈልጋለን፤ በመሆኑም በያዝነው በጋ አና በመጪው የበልግ ወቅቶች የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል የሚያስችሉዎትን በቅደም ተከተል የሚተገበሩ አራት ተግባራትን እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡
- የፀሃይ መከላከያ ቅባት ይጠቀሙ
ፀሃይ ቆዳችን ላይ ያለዉን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ የፀሀይ መከላከያ ቅባቶች ከፍተኛ አስተዋጽዎ አላቸዉ ፡፡ ቆዳችን በፀሃይ የመጎዳት ዕድሉ በከፍተኛ ቦታዎች ወይም በደጋ አካባቢ ይጨምራል፡፡ ስለሆነም ከቤት የመዉጣት እቅድ ካለዎት የፀሃይ መከላከያ ቅባት መቀባትዎን ያረጋግጡ፡፡
- ለእጅዎ ጥንቃቄ ያድርጉ
የእጅዎ ቆዳ በጣም ስስ፣ በቀላሉ የሚጎዳ እና ሁልጊዜም ማለት ይቻላል፣ ለጉዳት ተጋላጭ ነው፡፡ ለዚህም ነው የቆዳዎን የጉዳት መጠን ከሚያመለክቱ የሰውነት ክፍሎች አንዱ የሆነው፡፡ በእጅዎ የተለያየ የቤት ቁሳቁሶች እንዲሁም የልብስ ጽዳት ሲከዉኑ ጎንት ይጠቀሙ ፡፡ የእጆችዎን የቆዳ እርጥበትም ይጠብቁ፡፡
- የሚለብሷቸው አልባሳት ከተሰሩባቸው ነገሮች ጋር በተያያዘ ተገቢውን ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
እንደ ሱፍ፣ ናይለን እና ፖሊስተር ያሉ ልብስ የሚሰራባቸው ነገሮች ሰውነታች|ንን ሊያሳክኩ እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል? በጥጥ (በኮተን) የተሰሩ ልብሶችን በአንጻሩ ይህን ችግር አያስከትሉም ይህም በማከክ አማካኝነት ከሚመጣ የቆዳ ችግር ይከላከላል፡፡
- እርጥበት እንዲሰጡ በተሰሩ ምርቶች ብቃት ይተማመኑ
ቆዳዎ ከድርቀት ያመልጥ ዘንድ በሄዱበት ሁሉ ሎሽን እንዳይለይዎ እንመክርዎታለን፡፡ Vaseline Intensive Care lotions የቆዳን ተፈጥሮአዊ እርጥበት አፍኖ በመያዝ ቆዳዎን በደረቃማ ወቅት እርጥበቱን ጠብቆ እንዲቆይ ከሚያስችሉ የፔትሮሌየም ጀሊ ጥቃቅን ጠብታዎች የተሰሩ ናቸው፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ