ትኩረት በሚስበው ገፅታዎ ላይ ብርሃን ይዝሩበት
የእጅ እና እግርዎን ውበት ይጠብቁ
በሰውነት እንቅስቃሴ ራስን ወይም ሃሳብን መግለፅ እጅግ አስፈላጊ የግንኙነት አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በምናገኛቸው ሰዎች ዘንድ ስለራሳችን አዎንታዊ ምስል ለመፍጠር ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ለዚህ ነው የእጆችዎን፣ የእግሮችዎን እና የጥፍሮችዎን ውበት በመጠበቅ ጥሩ ስሜትን መፍጠር ሁልጊዜም አስፈላጊ የሚሆነው፡፡ ለምን ቤትዎ ውስጥ የራስዎን የቆዳ ርጥበት መጠበቂያ አያዘጋጁም? አዘገጃጀቱ ቀላል ከመሆኑም በተጨማሪ እጆችዎን እና እግሮችዎን እንደሃር ለስላሳ ያደርጋቸዋል፡፡ በቀላሉ 1 ስኒ የኮኮናት ቅቤ፣ 1 የሻይ ስኒ የቫይታሚን ኢ ፈሳሽ እና 6 የወይን ጠጅ አበባ ዘይት ጠብታዎችን ቀላቅለቀው ያዘጋጁት፡፡ ለመነጋገር የከንፈራችንን ያህል እጆቻችንንም እንጠቀማለን – ስለዚህ እጆችዎ ትኩረት የሳቡት ለትክክለኛ ምክንያት መሆኑን ርግጠኛ ይሁኑ፡፡
ፀጉርዎን ይንከባከቡ
ፀጉርዎ በዝናቡም በፀሃዩም፣ ቀንም ሆነ ማታ ተውበው ከሚታዩባቸው የሰዉነት ክፍልዎ አንዱ እና ዋነኛው መሆኑን ያስታውሱ – ስለዚህ ፀጉርዎ ምርጥ እንክብካቤ ይገባዋል፡፡ ይህን የራስዎን ዘውድ ቢያሻዎ ቁልቁል በሚምዘገዘግ ውብ ስታይል፣ ቢያሻዎ ወደላይ ሰብሰብ ተደርጎ በተሰራ ልዩ ስታይል እያስዋቡ ከፀጉር ጋር በተገናኘ ያለዎትን የትኛውንም ጥርጣሬ ያስወግዱ፡፡ በአማራጭነት በራስዎ ማዕድ ቤት ውስጥ በሚገኙ ግብዓቶች የራስዎን ቤት-ሰራሽ የፀጉር ርጥበት መጠበቂያ ቅባት ማዘጋጀት ይችላሉ! ይህን ተግባር ግማሽ አቡካዶ፣ ሩብ ስኒ ማየኒዝ፣ 2 የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ቅቤ እና 1 የሾርባ ማንኪያ ማር በመቀላቀል ይጀምሩት፡፡ እነዚህ ግብዓቶች የተቀላቀሉበትን ውህድ ወደጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ይገልብጡት እና ለሁለት ደቂቃ እንደዕንቁላል ይምቱት፡፡ ከዚያ በዚህ አዲስ ቅባት ርጥብ ፀጉርዎን ይቀቡ፡፡ ከዚያ ፀጉርዎን በሻወር ኮፍያ ይሸፍኑ እና ለግማሽ ሰዓት ያቆዩት፡፡
ቆዳዎን ያንን ውብ አንፀባራቂ ገፅታ ያጎናጽፉት
ቆዳዎ ያንፀባርቃል፤ ፀጉርዎ ያብረቀርቃል፤ እርስዎም ሙሉ ኩራት እና በራስ የመተማመን ስሜት ተሰምቶዎታል – ለዚህ የሚጠበቅብዎ ውበትን በሚፈነጥቁ ግሩም የውበት መጠበቂያዎች ማራኪ ገፅታዎን ማጉላት ብቻ ነው፡፡ ደረጃዎን ጠብቀው ፈታ ላለ ገፅታ ትንሽ የአይን ሻዶ፣ የተመጠነ ኩል፣ በትንሹ ስፓርክል ያለው ረጠብ የሚያረግ ግሩም የከንፈር ቀለም ይጠቀሙ፡፡ በውጤቱም ሰዉን ሁሉ ከፍጥነት ርምጃ የሚገታ፣ ልብ የሚያስደነግጥ ፈገግታ ይላበሳሉ፡፡
ልብስዎ ራሱ ይናገር
የሚያቁነጠንጥ ውበት አድናቂም ሆኑ ረጋ ያለ ዘመናዊ ማንነት፣ ሴትነትዎን የሚያደምቅ አለባበስን ምርጫዎ ያድርጉ፡፡ በራስ መተማመንዎን እና ርግጠኝነትዎን ለመግለፅ እና ስብዕናዎን በደንብ አጉልቶ ለማውጣት የሚረዳዎትን ልብስ ይልበሱ፡፡ የጊዜው ፋሽን ከሆኑ መነፅሮች የተመቸዎትን ይሞክሩ፡፡ መነፅር ፊትዎን ፍሬም ለማድረግ እና አይኖችዎን ከፀሐይ ብርሃን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የፋሽን ግብዓቶች በተለየ በራስ የመተማመን ስሜት እና ደፍሮ የወጣ ውበትን አጉልቶ ለማሳየት ይረዳል፡፡
መዓዛዎ እንደውብ ገፅታዎ
ለኔ ብቻ የሚሏትን የመዋቢያ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሟት፤ ቆዳዎን ከ LUX Range በርካታ አማራጮች በአንዱ እና እርስዎን በሚመችዎ የውበት መጠበቂያ ሳሙና ይንከባከቡት፡፡ በሰዎች ዘንድ እንዲታወሱ ለማድረግ እጅግ ከሚመረጡ መንገዶች አንዱ የሰውነት መዓዛ ነው፡፡ የነበሩበትን ክፍል እርስዎ ለቀው ሲወጡ የሰውነትዎ መዓዛ ጣፋጭ ማስታወሻ ሆኖ ዘለግ ላለ ጊዜ በዚያው ይቆያል፡፡ የሰዓት ማሰሪያ የእጅዎን ክፍል፣ አንገትዎን እና የጆሮዎችዎን ጀርባ ሽቶ ይቀቡ፡፡ አትኩረትን ወደሚያገኙበት እና ዕይታን ወደሚጋብዙበት ቦታ በሚያመሩበት አፍታ ጣፋጭ መዓዛዎ ልዩ የአድራጊነት ሃይል ሲያላብስዎ ይሰማዎታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ