የአጋጣሚ ጭውውት ጥበብን ለመካን 6 ጠቃሚ መላዎች
በገበያ እንደርስዎ ካሉ ሸማቾች ጋር፣ በመዝናኛ ቦታዎች ከሚዝናኑ ቢጤዎችዎ ጋር፣ መጓጓዣዎች ላይ ከጎንዎት ከተቀመጠ ሰው ጋር እና በሌሎች ቦታዎች ከሰዎች ጋር የሠላምታ ቃላት መለዋወጥ እንዲሁም የአጋጣሚ ጭውውት ማድረግ የሚቸግርዎት ዐይናፋር ዐይነት ሰው ነዎት! ግዴለም አይጨነቁ፡፡ ይኽ ብዙ ሰዎችን ምቾት የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ተከታዮቹን 6 ጠቃሚ መላዎች ይተግብሩና ጨዋታ አዋቂ ይኹኑ!
ጆሮ ይስጡ/በጽሞና ያድምጡ
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች መሰማትን ይፈልጋሉ፤ ይወዳሉ፡፡ ያድመጧቸው፡፡ ትኩረትዎን በነሱ ላይ አድርገው አግባብ ያላቸው ጥያቄዎች እየጠየቁ በጥሞና ይከታተሏቸው፡፡ ልብ ይበሉ፤ ራስን በአዎንታ መነቅነቅ ብቻ በቂ ላይኾን ይችላል፡፡
በጭውውት መሐል ፍላጎት ያሚያነቃቁ ጥያቄዎች ጣል ያድርጉ
የጭውውትን ርዕስ ከተለመዱት ዓይነት የዕለት ተዕለት ጉዳዮች የተለየ ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሌላውን ሰው ‹‹ልክ ነው››፣ ‹አዎ››፣ ‹‹አይደለም››፣ ‹‹አይ አይመስለኝም›› እና መሠል አጭር ምላሾችን በመሰንዘር እንዲገደብ የሚገፋፉ የጭውውት ጥያቄዎችን ላለማዘውተር ይጠንቀቁ፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነት ጥያቄዎች የጭውውትን ተፈጥሯዊ ፍሰት ይገድባሉ፡፡ ይልቅ ሌላውን ሰው በጥልቀት እንዲያስብ እንዲሁም ደግሞ ዘና እንዲል የሚያደርጉ የንግግር ርዕሶችን እና ጥያቄዎችን ለመጠቀም ይሞክሩ፡፡
ዘና ይበሉ
የፊትዎ ገጽታ የአጋጣሚ ጭውውት ዋናው አካል ነው፡፡ ሌላው ቢቀር በፊትዎ ላይ የሚገለጠው ኹነት ትክክለኛ ስሜት ከታከለበት ቤትዎን ሲያጸዱ የገጠመዎት አንድ ትንሽ አጋጣሚ እንኳ ሰዎችን እጅግ ሊያዝናና ይችላል፡፡ ፈገግ ይበሉ፤ አኳኋንዎም በመልካም ስሜት ውስጥ እንዳለ ሰው ይሁን፤ ያንጊዜ የበለጠ አዝናኝና ለአጋጣሚ ጭውውት ቀለል ያሉ ሰው ይሆናሉ፡፡
ሌላው እስኪያደርገው አይጠብቁ፤ እርስዎ ይጀምሩት
የአጋጣሚ ጭውውት ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች እንደሚደንሱት ዳንስ፤ በዚያም ውስጥ በስልተ-ምት (rhythm)ለመናበብ እንደሚሞክሩት ልክ እንደዚያ ዐይነት አድርገው ይዩት፡፡ በዳንስ የመጀመሪያውን የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ልዩ ምትኃታዊ ኃይል አለው፡፡ ያኔ ሌላኛው ሰው እርስዎን ለመቅረብ፣ ለመቀበል እና (በዳንስ እንቅስቃሴ ብንወስደው ደግሞ) ከእርስዎ ጋር ለመናበብ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ እርስዎም ለመጀመሪያው የሰውነት እንቅስቃሴ ሌላኛው ሰው የሰጠውን ምላሽ በመገንዘብ የጭውውቱን አካሄድ መቃኘት ይችላሉ፡፡
በራስዎ ይተማመኑ፤ ቀና ይኹኑ
ሌሎች ከእርስዎ ጋር ሊጨዋወቱ እንደሚፈልጉ እና እንደሚችሉ ቀና ሐሳብ ይኑርዎት፡፡ ከሕይወትዎ ለሌሎች ሊያካፍሉት የሚችሉት እና የሚገባ በርካታ ገጠመኞች እንዳለዎት ይረዱ፡፡ ራሳችንን እንዲሁም ነገሮችን የምናይበት መንገድ በኹነቶች ውጤት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡
ላከስ መላ፡ ከእንቡጥ ነጭ አበባ የተቀመመውን ላክስ የገላ ማለስለሻ ሳሙና Lux Soft Caress ይጠቀሙ፡፡ ላክስ የገላ ማለስለሻ ሳሙና በራስ መተማመንን በማበረታታት ጎልተው እንዲታዩ፣ ነጥረው እንዲወጡ ያደርግዎታል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ