ቫዝሊን በመጠቀም የቆዳ ድርቀትን ይሰናበቱት
ሁሉም ሰው የቆዳ ድርቀትና መሰነጣጠቅ ሊያስቸግረው ይችላል፡፡ ነገር ግን በቆዳ ድርቀት አማካይነት የሚከሰተው “አመድ” መሰል ገፅታ ጠቆር ያለ ቆዳ ባላቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ይጎላል፡፡ የቆዳ ድርቀት በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታል፡፡ ቆዳዎ ልዩ እንክብካቤ የሚያስፈልገው በበጋ ወቅት ብቻ አይደለም፡፡ በቂ መካላከያ ሳያደርጉ ከቤት ውጪ በመስራት ወይም በአንዳንድ ሳሙናዎች እና የፅዳት መጠበቂያ ውጤቶች ውስጥ ባሉ ጎጂ ኬሚካሎች አማካይነት ቆዳዎ ሊጎዳ ይችላል፡፡
ቫዝሊን ደረቅ ቆዳን የሚታደጉ በርካታ ምርቶችን አዘጋጅቶ ለገበያ አቅርቧል፡፡ Vaseline Cocoa Glow የደረቀ ቆዳዎን በማለስለስና ተፈጥሯዊ ወዙን በመመለስ እርጥበቱን እንዲጠብቅ ያደርግልዎታል፡፡ Vaseline Dry Skin Repair ደግሞ ከቆዳዎ የሚወጣውን እርጥበት አፍኖ በማስቀረት ቆዳዎን በሚገባ ይታደግልዎታል፡፡
Vaseline Men የወንዶች የቆዳ ቅባት የወንድ ቆዳ ለሚያስፈልገው ልዩ እንክብካቤ እንዲሆን ተብሎ በልዩ መንገድ የተሰራ ቅባት ነው፡፡ ይህ ሎሽን ቆዳን ቀዝቀዝ በማድረግ እና በፍጥነት ወደቆዳ በመስረግ ለወንዶች የተስተካከለ የቆዳ መልክ ያጎናፅፋል፡፡
በበጋ ወቅት የቆዳዎን ርጥበት ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥቆማዎች ያጢኑ፡
- ቀኑን ሙሉ ብዙ ውሃ ይጠጡ፡፡
- ሰውነትዎን በጣም በሞቀ ውሃ አይታጠቡ፡፡ በጣም በሞቀ ውሃ ሲታጠቡ ቆዳዎ ተፈጥሯዊ ቅባቱን ያጣል፡፡
- አቡካዶ የተፈጥሮ ቅባቶች ሁነኛ ምንጭ በመሆኑ ቢጠቀሙት ከውስጥ የቆዳዎን ርጥበት ይጠብቅልዎታል፡፡
- የተሰነጣጠቀ ተረከዝን፣ የሻከረ የክንድ መታጠፊያን እና ደርቆ የደደረ እጅን ለማለስለስ ቫዝሊን ፔትሮሊየም ጀሊን ይጠቀሙ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ