በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳ እንክብካቤ
ቆዳዎ በፀሐይ እንዲቃጠልና ከዚህ አልፎም ውሃ እስኪቋጥር ለፀሐይ ብርሃን ማጋለጥ በቆዳ ካንሰር የመያዝ ዕድልዎን ይጨምረዋል፡፡ በቆዳ ካንሰር ማሕበር መረጃ መሰረት በልጅነት ወይም በወጣትነት ጊዜ ያጋጠመ በፀሐይ ቃጠሎ ምክንያት የቆዳ ውሃ መቋጠር በሕይወትዎ የኋላ ምዕራፍ ሜላኖሚያ (ከቆዳ ካንሰር ጋር የተያያዘ በሽታ አምጪ ዕጢ) የመፈጠሩን ዕድል በእጥፍ ይጨምረዋል፡፡
የፀሐይ ቃጠሎን መከላከል
ከቤት ውጭ በሚሆኑበት ወቅት ከለላ የሚሰጥ ልብስ በመልበስና ቆዳዎን በትክክለኛ ሰን ስክሪን በመቀባት ቆዳዎን በፀሐይ ብርሃን ከሚፈጠር ቃጠሎ መከላከሉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከጥዋቱ 5፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ የፀሐይ ጨረር ከፍተኛ ኃይል የሚኖረው በመሆኑ በዚህ ሰዓት ውስጥ ከፀሐይ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ እንዳይኖር ይጠንቀቁ፡፡
የፀሐይ ቃጠሎን ማከም ስለሚቻልበት ሁኔታ
የፀሐይ ቃጠሎ በቆዳ ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ማንኛውንም የሕመም ስሜት ለማስታገስና ቆዳ እንዲያገግም ለማገዝ ትክክለኛውን የቆዳ ሕክምና መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በቀዝቀዛ ገላ መታጠቢያ ውስጥ ከ10 እስከ 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ሰውነትዎን ይንከሩ፡፡ ቀዝቃዛው የሙቀት መጠን ሕመሙንና ጥዝጣዜውን ሲያስታግስ ውሃው ደግሞ የፀሐይ ቃጠሎውን ያስታግሳል፡፡ ጠረን ያላቸውን የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች፣ አረፋ፣ የመታጠቢያ ጨው ወይም ቅባት አይጠቀሙ፣ ቆዳዎንም በሳሙና አይታጠቡ፤ እነዚህ ምርቶች በሙሉ ቆዳውን ይበልጥ ሊያስቆጡት ይችላሉ፡፡ ሰውነትዎን በፎጣ አያድርቁ – ከዚህ ይልቅ ሰውነትዎ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ በአየር እንዲደርቅ ያድርጉ፡፡
አሎይ (Aloe) ወሳኙ የቆዳ ማከሚያ ነው፡፡ ሕመምን ያስታግሳል፣ ቆዳን ያለሰልሳል እንዲሁም ያርሰዋል፡፡ አሎይ (Aloe) ለቆዳ የፈሳሽ መተካትን ስራ የሚሰራ ሲሆን በፀሐይ ብርሃን ጨረር ለተቃጠለ ቆዳ ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ የተወሰነ መጠን ያለው Vaseline aloe soothe ሎሽን ቢጠቀሙ ወዲያውኑ ሕመም የማስታገስ ባሕርይ ያለው ሲሆን በጣም የሚፈለገውን የሕመም እፎይታንም ያስገኛል፡፡ የማጣበቅ ባሕርይ የሌለው ሲሆን ቆዳም ቀዝቀዝና ረጠብ እንዲል ያደርገዋል፡፡
የፀሐይ ቃጠሎ በሰውነት ውስጥ የሚገኝን ፈሳሽ ሊያሟጥጥና የራስ ምታትና የማቅለሽለሽ ስሜትን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከፀሐይ ቃጠሎ በሚያገግሙበት ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመጠጣት ከሰውነትዎ የወጣውን ፈሳሽ መተካት አስፈላጊ ነው፡፡
የፀሐይ ቃጠሎ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ከቤት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ፣ ጥላ ስር መሆንዎንና ቀለል ያለና ከለላ ሊሰጥ የሚችል ልብስ በተጎዳው የሰውነት ክፍል በኩል መልበስዎን ያረጋግጡ፡፡ ማንኛውም ተጨማሪ ጉዳትን ለመከላከል ቆዳዎን በ SPF 50 ይጠብቁ፡፡ በፀሐይ በተቃጠለው ቆዳዎ ውስጥ ሰርጎ የገባ ማንኛውም አልትራ ቫዮሌት ጨረር ቆዳ ውሃ እንዲቋጥርና የበለጠ የምቾት ማጣት ስሜት እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ያስታውሱ፡፡
የፀሐይ ቃጠሎን በተመለከተ ከማዳን ይልቅ አስቀድሞ መከላከሉ የተሻለ ነው፡፡ በቀጣይም ከቤት ውጭ ፀሐይ ባለበት ሰዓት ይህንን ያስታውሱ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ