በአለባበስዎ በራስ የመተማመን ስሜትዎን የማዳበር ጥበብ
ሁላችንምመ በአካላዊ ቁመናችን ሙሉ በሙሉ የምንተማመን ሰዎች እንድንሆን እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ይህን በራስ የመተማመን ስሜት መፍጠር ሁልጊዜም ቀላል አይደለም፡፡ ሊለብሱት ሲያልሙት የኖሩትን ልብስ ለብሰው እንኳን ቢሆን ውስጥዎ አንዳች ነገር ሹክ እያለ ስለመረጡት አለባበስ ትክክለኛነትና ውበት እንዲጨነቁ ያደርግዎታል፡፡ አንዲት ሴት በግብዣ ቀሚሷ አጊጣም ሆነ በመሮጫ ልብሷ ሆና ደስ የሚል ስሜት ሊሰማት እንደሚገባ እናምናለን፡፡ በሰውነትዎ አቋም እንዲተማመኑ የሚረዱዎትን የተወሰኑ ጥቆማዎችን እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡
በራስ መተማመንን ለማጉላት የሚመረጥ አለባበስ
- ሲጫሟቸዉ ምቾት የሚነሱ ነገር ግን በጣም የሚወዷቸዉ ጫማዎች ወይም ደግሞ በጣም የሚወዱት ግን ጥብቅብቅ የሚያረግዎና የማይመችዎ ቀሚስ አለዎት? እነዚህን ለመቀየር ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡ በማይመችዎት አልባሳት እየተቸገሩ ለመቆየት ሕይወት ራሷ አጭር ናት፤ በራስ መተማመንዎ የሚጎላው ምቾትን በሚሰጥዎ አለባበስ አምረው ሲታዩ ነው፡፡
- ክንድዎንና ብብትዎን የሚያሳዩ ልብሶች ሲለብሱ የመጋለጥ ስሜት ስለሚሰማዎት በራስ መተማመንዎ ይቀንሳል፡፡ በራስ መተማመንዎን ለመጨመር ከላብ ጠብቆ አስፈላጊዉን እርጥበት የሚሰጥዎትን deodorant ይጠቀሙ፡፡
- የስነልቦና ተመራማሪዎች የምንለብሰው ልብስ ከስሜታችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ይናገራሉ፡፡ በራስ የመተማመን ስሜትን በአለባበስ ለማጉላት አንዱ መንገድ የራስ መተማመናቸው ከፍተኛ የሆነ የሚሏቸውን ሰዎች ወደምናብዎ በማምጣት እና እነሱን በማሰብ እንደነሱ ለመልበስ መሞከር ነው፡፡ የተከበሩ የንግድ ባለሞያም ሆኑ ዝነኛ ሴት በራስ የመተማመን ባህሪዎን ትክክለኛውን አለባበስ በመምረጥ ሊያጎለብቱት ይችላሉ፡፡
- ለእራት ቀጠሮዎም ሆነ ከሴት ጓደኞችዎ ጋር ሻይ ቡና ለማለት ቆንጅዬ ጥቁር ቀሚስ ለብሶ መምጣት በብዙዎች የሚወደድ አለባበስ ነው፡፡ ሆኖም አንድ ነገር ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ ጥንቃቄ ካላደረጉ ባለደማቅ ቀለም ልብስዎን deodorant ሊያበላሽብዎ ይችላል፡፡ ስለዚህ ጠቆር ያለ ልብስ በመልበስና deodorant በልብስዎ ላይ ነጭ ምልክት እንዳይተው በማድረግ በራስ የመተማመን ስሜትዎን አጉልተው ማውጣት ይችላሉ፡፡
- ሰውነትዎን ይውደዱ፡፡ ሁላችንም ሰውነታችንን ወደተሻለ አቋም ለመቀየር እንመኛለን፡፡ ሆኖም ባለዎት ሰውነት ላይ ያለዎትን በራስ የመተማመን ስሜት ማጎልበት ምርጥና ውጤታማ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ አካልዎን ይውደዱት፤ በማንነትዎ ይኩሩ – ምክንያቱም እውነተኛ ውበት ማለት ይህ ነውና፡፡
- የሚለብሱት ልብስ በቁጥሩ የኔ ልክ አይደለም ብለው ብዙ አይጨነቁ፡፡ ሱቆች በተመሳሳይ ቁጥር የተለያየ ልኮችን ይይዛሉ፡፡ ልብሱ ላይ የተፃፈው የልክ ቁጥር ምንም ይሁን ምን ዋናው ልብሱ ለእርሶ ልክና የተስማማ መሆኑ ነዉ፡፡ ያስታዉሱ! ልብስ እንዲያምርብዎ የሚያደርጉት እርስዎ እንጂ በልብሱ ላይ ያለው የልክ ቁጥር አይደለም፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ