በሮዝ አበባ ማራኪ ሃይል ይደሰቱ
በርዎን ዘግተው፣ ሞባይልዎን ወይም ላፕቶፕዎን አጥፍተው አብልጥው በሚወዱት ስፓ እና የመዋቢያ ምርቶች እየተቆነጃጁ ዘና ብለው ከሚያሳልፉት የምቾት ጊዜ የበለጠ ደስ የሚያሰኝ ምን ነገር ሊኖር ይችላል? የጊዜ ገደብ የለብዎ፤ ከስራዬ ያዘናጋኛል ብለው አይጨነቁ፤ ራስዎን ዘና የሚያደርጉበት ጊዜ ነው፡፡ ለዚህ አይነት ልዩ ተዝናኖት የተለየ ጊዜን መጠበቅ አያስፈልግዎትም – የሮዝ አበባ ማራኪ መዓዛ ወዲያውኑ ይሄን ልዩ ስሜት ሊፈጥርልዎ ይችላል፡፡ ለመሆኑ ሮዝ አበባ ዘና የምታደርገን ለምንድነው? አበባ ንቅት፣ ፍክት አድርጎ እንደንግስት እንዲሰማን የማድረግ ምስጢሩ ከምን የመጣ ይሆን?
ቆንጆ አበባ
ሮዝ አበባ 35 ሚሊዮን አመታትን ያስቆጠረ የረጅም ጊዜ አስደናቂ ታሪክ አላት፡፡ በቆንጆ ሽታዋ ምክንያት የሮዝ አበባ ሁልጊዜም የመልካም መዓዛዎች ንግስት በመባል ትታወቃለች፡፡ በጉልህ፣ ጣፋጭና ማራኪ የአበባ ሽታዋ የተነሳ መዓዛዋ እንደ ሮዝ አበባ ጣፋጭ እንዲሆንላት የማትፈልግ የትኛዋ ሴት ናት? ሮዝ አበባ መንፈስን አድሳ በአእምሮአችን ወደገነት ዓለም የመውሰድ ሃይል አላት፡፡
የአበቦች ንግስት
በሁሉም ባህሎችና ስልጣኔዎች ውስጥ የሚነገሩ የቆንጆ ሮዝ አበባ ታሪኮች አሉ፡፡ ሮማውያን ምንጣፋቸውላይ ጎዝጉዘው እንግዶቻቸውን ዘና ለማድረግ ሮዝ አበባ ያመርቱ ነበር፡፡ ከዚያም አልፎ መዓዛው እንግዶቻቸውን ዘና እንዲያደርግላቸውና ተፈላጊነታቸው የመጨመር አይነት ስሜት እንዲሰማቸው በወይንና በቢራ ላይ አበባ ያንሳፍፉ ነበር፡፡ በግሪክ ትውፊት ሮዝ አበባ ‘የአበቦች ንግስት’ ትባላለች፡፡ ይች አበባ ለረጅም ዘመን በህዝቦች ዘንድ የፍቅር፣ የውበት፣ የስሜትና የምቾት ተምሳሌት ተደርጋ ስትታይ ኖራለች፡፡ ከሮዝ አበባ በላይ በታዋቂ አባባሎችና ውብ ቃላት የተወደሰ ሌላ የአበባ አይነት ይኖር ይሆን?
ጤናማ ድምቀትና ፍካት
ሮዝ አበባ በንጥረነገሮችም የበለፀገ ሲሆን ለመቶዎች ዓመታት የመዋቢያ ምርቶች ዋነኛ ግብዓት በመሆን አገልግሏል፡፡ ሮዝ አበባ ለቆዳ ጤናማ ድምቀት በሚሰጡ እንደ ፍላቮኖይዶች፣ አንቲኦክሲዳንቶች፣ ታኒኖች እና ቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ዲ፣ ኢ እና ቢ3 ባሉ ንጥረነገሮች የበለፀገ ነው፡፡ ቆዳዎን ለጋ፣ ጤናማ አድርጎ ከማስዋብ በተጨማሪ ጣፋጭ መዓዛ እንዲኖረው የሚያደርግ ልዩ አበባ ነው፡፡
ድንቅ ፈሳሽ
ንፁህ የሮዝ አበባ ቅባት በርግጥም የአለማችን ውድና ድንቅ ንጥር ነው፡፡ ምርጦቹ የሮዝ አበባ መዓዛዎች የሚገኙት በፀሃይ ብርሃን ወቅት ከተለቀሙ አበቦች ነው፡፡ የሚያስደስት መዓዛ ላለው የሮዝ አበባ ቅባት ፀሃይና ሙቀት ዋነኛ ግብዓቶቹ ናቸው፡፡
አንድ ሊትር ምርጥ የሮዝ አበባ ቅባት ለማምረት ሶስት ቶን ትኩስ የሮዝ አበባዎች እንደሚያስፈልጉ ያውቁ ኖሯል? የቤትዎን ስፓና አልጋዎትን ሳይቀር በሚሞላ የትኩስ ሮዝ አበባ መዓዛ ዘና እንደማለት ወይም ለረጅም ሰዓት ገላዎን በምርጡና የሮዝ አበባ መዓዛን በሚያጎናፅፍዎ የላክስ ሳሙናና የተፈጥሮ ቅባቶች እንደመታጠብ ምን የሚያስደስት ነገር ይኖራል? ሲጀመር ላክስ እርስዎን ማስዋቡንና ዘና ማድረጉን ያውቅበታል፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቹ የመዋቢያ ሳሙናዎቻችን ምቾትን ከሚሰጡት የሮዝ አበባ ንጥሮች የተሰሩ መሆናቸውን የምናረጋግጥልዎ፡፡ ስለሚገባዎት ራስዎን እንዲንከባከቡት እንመክርዎታለን፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ