በራስ መተማመንሽ ከውበትሽ ይመነጫል!
የሰውነትሽን ቆዳ በሚገባ ተንከባከቢው!
ሰዎች በየትኛውም ቦታ ሲያገኙሽ መጀመሪያ የሚያዩት ቆዳሽን ነው፡፡ ለዚህ ነው ቆዳሽን መንከባከብ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው፡፡ ይህን ማድረግሽ በራስሽ ላይ ያለሽ እምነት እንዲጨምር እና ጥሩ ስሜት እንዲሰማሽ ያደርጋል፡፡ ቆዳሽን በጥንቃቄ መንከባከብሽ ውበትሽን በማጉላት በየትኛውም ቦታ ደምቀሽ እንድትታዪ ያስችልሻል፡፡ የቫዝሊንን Intensive Care Cocoa Glow ሞክረሽው ታውቂያለሽ? ይህ ተወዳጅ ሎሽን ደረቅ ቆዳን በሚገባ በማለስለስ ተፈጥሯዊ እና የሌሎችን ዓይን የሚስብ አንጸባራቂ ድምቀት ይለግሳል፡፡ አሁን ለVaseline Intensive Care Cocoa Glow ምስጋና ይግባውና ራስሽን በለስላሳ ቆዳ ማስዋብ ትችያለሽ፡፡
ለስላሳ የሰውነት ቆዳ ያስፈልግሻል!
ገላሽን ለብ ባለ ውኃ ስትለቃለቂ ሰውነትሽንና አእምሮሽን ዘና ታደርጊያለሽ፡፡ በተለይ “ስቲም” መግባትሽ የሞቱ የቆዳ ላይ ሴሎችን በማስወገድና ከቆዳ ሥር የተወሸቁ መርዛማ ነገሮችን በማጽዳት ቆዳሽ አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
በሙቅ ውኃ ሰውነትሽን ከተለቃለቅሽ በኋላ ሰውነትሽን በVaseline Aloe Soothe Intensive Care ሎሽን ለስለስ አድርገሽ ታሽዋለሽ፡፡ የሰውነት ቆዳን ለማደስ እና ልስላሴውን ለመጠበቅ የሚረዳ ንጹህ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር የያዘው ይህ ቫዝሊን ሎሽን ቆዳሽ ጤናማ፣ ውብ እና ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
በማራኪ መዓዛ ስሜትሽን አድሺ!
የምትወጂውን ሽቶ በመቀባት ለራስሽ የተወዳጅነትን ስሜትን መፍጠርና በሚጥም መዓዛ ውስጥ መቆየትን አትርሺ! ሽቶውን እጆችሽ እና አንገትሽ ግራ እና ቀኝ ክፍል ላይ ወይም ደረትሽ አካባቢ መቀባት ትችያለሽ፡፡ የምትቀቢው ሽቶ መዓዛ ከግማሽ ቀን የማይዘል ወይም ቶሎ የሚጠፋ እየሆነ ተቸግረሻል? እንዲያ ከሆነ የቫዝሊንን Original Petroleum Jelly እንድትጠቀሚ እንመክርሻለን፡፡ የቫዝሊን ሎሽንን በአነስተኛ መጠን እጆችሽ እና አንገትሽ ሥር ብትቀቢ ሙሉ ቀን ያለተጨማሪ ሽቱ ከማራኪ መዓዛ ጋር መቆየት ትችያለሽ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ