በማዕድ ቤት መጠቀሚያዎች የሚፈቱ 5ቱ የ DIY የውበት ሚስጥሮች
ምግብ ለማብሰል፣ ለማጣፈጥ ወይም ውብ ቤትዎን ለማፅዳት ይጠቀሟቸዋል፡፡ ሆኖም አንዳንዴ እነዚህ የማዕድ ቤት መጠቀሚያዎች ጥሩ፣ ቦርሳ-ገብ የመዋቢያ ዕቃዎችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ውድ ዕቃ መሸጫ ስፍራዎችን ይርሷቸውና አጠቃቀማቸው አፍታም የማይወስድብዎትን እነዚህን የማዕድቤት መጠቀሚያዎች ለመዋቢያ ይሞክሯቸው፡፡
አፕል ሳይደር ቪኔጋር
አንድ ጠርሙስ አፕል ሳይደር ቪኔጋር ቤትዎ ውስጥ ከሌለ ከአቅራቢያዎ ከሚገኝ ሱፐርማርኬት እንዲገዙ እንመክርዎታለን፡፡ የሚገርም የምግብ ማጣፈጫና የፅዳት ግብዓት ብቻ ሳይሆን ሰውነትን የማጥሪያ ፈሳሽም ነው፡፡ ከፅዳት በኋላና ቅባት ከመቀባትዎ በፊት ከተጠቀሙት ቆዳዎን ጥሩ መልክ ያላብሳል፡፡ በተጨማሪም የቆዳ ላይ ነጠብጣቦችን ያጠፋልዎታል፡፡
የኮኮናት ዘይት
የኮኮናት ዘይት በተፈጥሮ ባህሪያቱ፣ ለጤና ባለው ጠቀሜታና በአጠቃላይ ተስማሚነቱ የሚገባውን ትኩረት አግኝቷል፡፡ የሜካፕ ማፅጃ በመጠቀም ፋንታ ጥጥ ወይም ለስላሳ ወረቀት ኮኮናት ዘይት ውስጥ በመንከር ሜክአፕም ሆነ በአይኖችዎ ሽፋሽፍት ላይ የተጠቀሙትን መዋቢያ ለማንሳት ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
ቀዝቃዛ ባለከረጢት አረንጓዴ ሻይ ቅጠል
ብዙዎቻችንን የዓይን እብጠት ያስቸግረናል፡፡ የዓይን እብጠት ካስቸገረዎ ይህ የውበት ምስጢር ርስዎን ይመለከትዎታል፡፡ ሁለት ሙሉ እርጥብ የአረንጓዴ ሻይ ከረጢቶች አርጥበው ካቀዘቀዙ በኋላ ከዓይንዎ አካባቢ ከታች (ወይም ከላይ) አድርገው ለአምስት ደቂቃ ያቆዩዋቸው፡፡ በሻይቅጠሉ ውስጥ ያሉት እብጠትን መከላከል የሚችሉ ነገሮች ድካም ያለባቸውን አይኖችዎን በማፍታታት እና ዕብጠቱን በማስወገድ ቀኑን ሙሉ አይኖችዎ ተገልጠውና ብሩህ ሆነው እንዲውሉ ያደርጋቸዋል፡፡
የገላ መታጠቢያ ፈሳሽ እና ቡናማ ስኳር
ቆዳዎን መፈግፈግ ፈልገው ነገር ግን መፈግፈግያው አልቆብዎ ከሆነ አንዱን የሚወዱትን የገላ መታጠቢያ ፈሳሽ ወስደው ከቡናማ ስኳር ጋር በማዋሃድ መላ ሰውነትዎን የመፈግፈጉን ተግባር ጥሩ አድርገው መከወን ይችላሉ፡፡ ምናልባት ስኳሩ ለቆዳዎ ጠጣርና ሻካራ ከሆነበት፣ ስኳሩን ለማቅለጥ ትንሽ የኮኮናት ዘይት ወይም ማር በመጨመር የመፈግፈጉን ተግባር ለስለስ ያለ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ስኳር በውስጡ የያዘው ተፈጥሯዊ አሲድም ለቆዳዎ ርጥበትና ልስላሴ ጠቀሜታ አለው፡፡
የሎሚ ጭማቂ
ብሩህና ደማቅ የጥፍር ቀለሞች ለሰመር ወቅት ተስማሚ ናቸው፤ ሆኖም አልፎ አልፎ ጥፍራችንን በከፊል ቢጫ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ጤናማ ያልሆነ ጥፍር ያስመስሉታል፡፡
ደግነቱ ጥፍርዎን በሎሚ ጭማቂ ውስጥ ነክረው ፅዱ ማድረግና ዳግም ወደጤናማ መልኩ መመለስ ይችላሉ፡፡ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ የሎሚ ጭማቂ ይሙሉና ቢጫማውን ጥፍር ለ10 ደቂቃ ያህል ጭማቂው ውስጥ ነክረው ያቆዩት፡፡ ከዚያ በርጋታ ጥፍርዎን በጥርስ ብሩሽ ሲወለውሉት ቢጫው ቀስ እያለ ሲለቅ ያዩታል! ይህን ሂደት ቢጫው ነገር በጥፍርዎ ላይ የቆየ ከሆነ ሁለት ጊዜ መድገም ያስፈልግዎት ይሆናል፡፡
የእርስዎ የቤት ውስጥ የውበት ምስጥሮች ምንድናቸው?
የላክስ ጥቆማ፡ እነዚህን ብልሃት የተሞላባቸውን የቤት ውስጥ የውበት ምስጢሮች በመጠቀም ያዳኑትን ወጪ አሁን እንደ ላክስ ቪልቬት ተች ያሉትን አስበልጠው የሚወዳቸውንና ጣፋጭ መዓዛ ያላቸውን ምርቶች መግዣ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ