ቅባታም ቆዳን መለየት
ሰውነታችን የቆዳችንን ጤናማነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ቅባትን ያመነጫል፡ ይሁን እንጂ፣ ቅባታምነቱ የበዛ የቆዳ ዓይነት ካለዎ፣ እነዚህ ቅባቶች ከሚያስከትሏቸው ችግሮች መካከል ከመጠን ያለፈ የቆዳ አንጸባራቂነት፣ የቆዳ መፈንዳት፣ የቆዳ መምገልና መደፈን ይገኙበታል፡፡ ቅባታም ቆዳ ሊኖራቸው የሚችሉ የሰውነት ክፍሎች ጀርባና ደረት አካባቢ ናቸው፡፡ ትክክለኛውን የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች መጠቀም በሰውነትዎ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ቅባታም ቆዳን በሚገባ ለማስተካከል ሊያግዝዎ ይችላል፡፡
ቅባታም ቆዳ ብዝውን ጊዜ የሚታየው በታዳጊ ወጣቶችና ዕድሜያቸው በሃያዎቹ አካባቢ በሚገኙ ሰዎች ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ በሰላሳዎቹና አርባዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎችም ከመጠን ያለፈ የቆዳ ቅባታምነትና የቆዳ መፈንዳት ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ ሆርሞኖችና ዘረ መሎች የቆዳን ቅባታምነት የሚያስከትሉ ሲሆን ሞቃታማና ርጥበታማ የአየር ሁኔታም እንደዚሁ ከመጠን ያለፈ ቅባት እንዲመነጭ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ቅባታም ቆዳ ያላቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ መጠነ ትልቅ የቆዳ እብጠት፣ በፊት ላይ በግልጽ የሚታይ አንጸባራቂነትና ተደጋጋሚ የቆዳ መምገልና የቆዳ መፈንዳት ችግር በፊት፣ በጀርባና በደረታቸው ላይ ይታይባቸዋል፡፡ ቅባታም ቆዳ ያላቸው ሰዎች ቆዳቸውን ማርጠብ የለባቸውም የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አለ፡፡ ተስማሚ የሆነና ለቅባታም ቆዳ ብቻ የተዘጋጀ የቆዳ እንክብካቤ ምርትን መጠቀም ቆዳዎንም እየተንከባከቡ የቅባት መመንጨት መጠንም እንዲቀንስ ሊያግዝ ይችላል፡፡
Vaseline aloe soothe የርጥበት መጠኑ አነስተኛ ስለሆነ፣ የማያሙለጨልጭና በፍጥነት ወደ ቆዳ ሰርጎ መግባት የሚችል በመሆኑ ለቅባታም ቆዳ የሚመከር ነው፡፡
ቅባታም ቆዳን ይቆጣጠሩ
ቅባታም ቆዳ ካለዎ፣ ጤናማ ቆዳ እንዲኖርዎ ከታች የተገለጹትን ዘዴዎች ይጠቀሙ፡፡
ቆዳዎን ንጽህና በአግባቡ ይጠብቁ
ፊትንና ሰውነትን በየቀኑ መታጠብ ቅባትም ቆዳን ሊፈጥሩ የሚችሉ የኤር በካዮችንና ላብን ለማስወገድ ያግዛል፡፡ ቆዳዎ እንዳይቆጣና የቅባት ማመንጨቱ መጠን እንዳይጨምር ፊትዎን አጥብቀው ከመፈተግ ይቆጠቡ፡፡
ጤናማ የአመጋገብ ልማድን ያዳብሩ
ቆዳችን የምንመገበውን ምግብ ያንጸባርቃል፡፡ በሟሟ ቅባት፣ በፋብሪካ በተቀናበሩ ምግቦችና በስኳር ውስጥ ያለ ምግብ የቆዳን ቅባታምነት ያባብሰዋል፡፡ መጠኑ የበዛ ትኩስ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን በየቀኑ መመገብ የቆዳዎን ሁኔታ የሚያሻሽል ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ ተክሎች ሴሎችን እየገነቡ ቆዳን ከውጫዊ ጥቃት የሚከላከሉ አንቲ ኦክሲዳንትስ እና ፋይቶኒውትሪንትስ በውስጣቸው ስለያዙ ነው፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያዘውትሩ
ጭንቀት ሰውነትዎ በጠኑ የበዛ ፈሳሽ እንዲያመነጭ ስለሚያደርገው እርሱም በተራው ቅባታም ቆዳና የቆዳ መፈንዳት ችግር እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ ዘወትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመስራት ጭንቀትን መቋቋም ይችላሉ፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ደም በሰውነት ውስጥ እንዲረጭ ስለሚያደርግ ኦክስጂን ወደ ቆዳ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
በቂ ውሃ ይጠጡ
በቀን የሚያስፈልገውን ስምንት ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ለሰውነትዎ ፈሳሽ እየሰጠ መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡ ይህን ልማድ ማዘውተርዎ ደግሞ አንጸባራቂና ውብ የሆነ ቆዳ እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ