ስለምትጠቀሚው ኮንዲሽነር ምናልባት ያላወቅሻቸው 7 ፍሬ-ነገሮች
ሻምፖ ጸጉርን በመልካም ውበትና መዓዛ ለማቆየት አስፈላጊ መኾኑ በሚገባ የሚታወቅ ነው፡፡ የጸጉር ኮንዲሽነርን በተመለከተ ግን አደናጋሪ ነገሮች አሉ፡፡ ስለ ኮንዲሽነር ጥቅም፣ መቼ መጠቀም እንዳለብሽ፣ ለደረቅ ወይስ ለርጥብ ጸጉር፣ በሙሉ ጸጉር ላይ የሚጠቀሙት ወይስ የጸጉር ሥርና ጫፍ ላይ ብቻ የሚቀቡት፣ ወዘተ … ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሞክረሽ ታውቂያለሽ?
አትጨነቂ! ስለ ኮንዲሽነር ማወቅ ያለብሽንና ለጸጉርሽ ጤናና ውበት የሚጠቅምሽን መረጃ አጠናቅረናል፡፡
7ቱ ፍሬ–ነገሮች፡
- ብታምኚም ባታምኚም ኮንዲሽነር ተጠቅመሽ በጸጉርሽ ላይ ለረጅም ሰዓታት እንዲቆይ ማድረግ አይጠበቅብሽም፡፡ ለረጅም ጊዜ ብታቆዪውም ወይም ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት ተቀብተሽው ብትተኚ እንኳ ውጤቱ ለአጭር ጊዜ ከምትጠቀሚው የተለየ አይኾንም፡፡
- ኮንዲሽነር መጠቀም ያለብሽ ሻምፖ ከተጠቀምሽ በኋላ ነው፡፡ ጥሩ ኮንዲሽነር፤ ለምሳሌ የኛ ምርት የኾነው ዶቭ ኢንቴንሲቭ ሪፔር ኮንዲሽነር፤ ለጸጉርሽ ከፍተኛ ክብካቤ የሚሰጠው ከታጠብሽ በኋላ ስትጠቀሚው ነው፡፡
- ኮንዲሽነር ጸጉርሽን ለመፍታትና ለማበጠር የሚረዳሽ አሪፍ መላ ነው፡፡ ለጸጉርሽ አንጸባራቂነት ከመስጠቱም በላይ ከምንጊዜውም በላቀ ወዛምና ለስላሳ ያደርገዋል፡፡
- ርጥብ ጸጉር፤ በተለይ ለማድረቅ ፎጣ ስትጠቀሚ በቀላሉ ለጉዳት ይዳረጋል፡፡ ኮንዲሽነር ለጸጉርሽ የውጪኛው ክፍል ከለላ በማድረግ ይህንን ጉዳት ይቀንሳል፡፡
- ኹለት ዐይነት ኮንዲሽነሮች አሉ፤ አንዱ ጸጉርሽን ተቀብተሽው የሚቆይ ሲኾን ሌላኛው ደግሞ ተጠቅመሽ ወዲያው የምትታጠቢው ነው፡፡ አስታውሺ – የመጀመሪያው ሌላኛውን የሚተካ አይደለም፡፡ መደበኛዎቹ ተጠቅመሽ ወዲያው የምትታጠቢያቸው ኮንዲሽነሮች የተወሰኑ ጉዳት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች በጸጉር ላይ በመተው ጸጉርሽን የማለስለስና ከጉዳት የመጠበቅ ተግባር ያከናውናሉ፤ ይህም ተቀብተሽ ከምታቆያቸው ኮንዲሽነሮች ጋር ተመሳሳይ ተግባር ያላቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ተቀብተሽ የምታቆያቸው ኮንዲሽነሮች ስስ ኾኖ ጉዳት ለማይችል እንዲኹም ከታጠበ በኋላ ለሚሸበሸብ ጸጉር መልካም መፍትሔ ናቸው፡፡
- ወዛም ይኹን ከርዳዳ፣ ጉንጉን ይኹን ብትን፤ ምንም ዐይነት ጸጉር ቢኖረው ኹሉም ሰው ኮንዲሽነር መጠቀም አለበት፡፡ ጸጉርን በኮንዲሽነር መንከባከብ ለጸጉር ደኅንነትና ውበት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለየጸጉር ዐይነቱ የሚኾኑ ኮንዲሽነሮች በገበያ አሉ፡፡ ለምሳሌ ለስስ ጸጉር የተዘጋጁ ኮንዲሽነሮች በቂ ተንከባካቢ ንጥረ ነገሮች ያላቸው ኾነው በልዩ የተዘጋጁ ሲኾኑ ጸጉር ሳይጎዳ አንጸባራቂ እና ለስላሳ ኾኖ እንዲቆይ ይረዳሉ፡፡
- ብዙ ሰዎች፤ ጸጉራችን የምንጠቀመውን ማንኛውንም ዐይነት ኮንዲሽነር ይላመዳል የሚል ዕምነት አላቸው፡፡ ይህ ልክ አይደለም፡፡ ይህ ዕውነትነት ያለው ከመሰለሽ ጸጉርሽ በዚህ ምክንያት ተቀይሯል ማለት ነው፡፡ በቶሎ ላኹኑ ጸጉርሽ ተስማሚውን ኮንዲሽነር ምረጪ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ