ሰልፊ በ5 ተከታታይ ተግባራት ምርጥ ፎቶ ያደርጉት
ዓለም በሰልፊ ፍቅር አብዷል፡፡ ለመሆኑ ሰልፊ ምንድነው? ሰልፊ በአብዘኛው በሞባይል ስልክ ካሜራዎ አንስተው በማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካይነት ለጓደኞችዎ የሚያጋሩት የራስዎ ፎቶ ማለት ነው፡፡
ማንኛውም ብርቱ የማህበረ-ገፅ ተጠቃሚ እንደሚያውቀው የራስዎን ማንነት ለማሳወቅ በብዙ ስታይሎች የተነሱ የራስ ፎቶዎች ወይም ሰልፊዎች ጋለሪ በእጅጉ ያስፈልጉዎታል፡፡ ከታዋቂዋ የሪያሊቲ ቲቪ ኮከብ ከኪም ካርዳሽያን (በቅርቡ ስለሰልፊ ባለ20 ዶላር መፅሐፍ ለገበያ ታቀርባለች) የሚከተሉትን ማነቃቂያ ሃሳቦች ይውሰዱና የሰልፊ ጠቢብ ይሁኑ
1. እያንዳንዱን ፎቶ ሲያነሱ እንዴት ትክክለኛውን ማዕዘን ወይም አንግል መጠበቅ እንዳለብዎት ይወቁ
ለሰልፊ የፎቶግራፍ ባለሙያው ራስዎ ነዎት፤ ስለዚህ ፎቶ የማንሳቱን ስራ ራስዎ ይመራሉ፡፡ ሰልፊ ለማንሳት ምርጡ አኳኋን ቀና እና ወደላይ ከፍ ብሎ መታየት ነው፡፡ ጭንቅላትዎን ወደጎን ዘንበል ያድርጉና ቅፅበታዊ የሰውነት ከፍታን ለመቀዳጀት አንገትዎን ወደፊት ወጣ ወይም ሰገግ ያድርጉት፡፡ ፎቶዎ ላይ የበለጠ ተፈጥሯዊ ማንነትዎን ለማየት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ትካሻዎትን በመጠኑ ወደፊት ወጣ ያድርጉት፡፡
2.ነፃ ይሁኑ
ጠቃሚ ነገር፡ ሰልፊዎች ተኮሳትረን የምንነሳቸው ፎቶዎች አይደሉም፤ ሳቅ የተመላባቸው እንዲሆኑ ይጠበቃል! ተኮሳትረን የተነሳናቸው ሰልፊዎች ብዙ ጊዜ የተዋጡ አይደሉም፡፡ የሚያምር ነገር በማድረግ ነፃነትዎ የሚጎላበትን የማንነትዎን ክፍል ያሳዩባቸው – ከት ብሎ መሳቅ፣ በእጅና በከንፈር የመሳም ምልክት ማሳየት – ነፃ ስሜትዎን የሚያጎላ የፎቶ ዳራ ወይም ባክግራውንድም ጥሩ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
3.ዋናው ዳራው ነው
‘ምርጥ ሰልፊዎች’ የሚባሉት ሰዎች አትኩሮትን የሚስቡ ነገሮች ሲያደርጉ፣ በዓለም ዙሪያ ሲጓዙ፣ ውብ የጥበብ ጋለሪ ሲጎበኙ ወይም በደማቅ ዝግጅቶች ላይ ሲሳተፉ የተነሷቸው ፎቶዎች ናቸው፡፡ በደምብ ይጠቀሙበት፤ ሰልፊ የሚነሱበትን ቦታ በብልሃት ይምረጡ፡፡ ደማቅ፣ ብሩህ ወይም ዓይን የሚስብ ዳራ ወይም ባክግራውንድ መንፈስን ለማደስና ፎቶውንም ብሩህ እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል፡፡
4. ‘በቂ’ ብርሃን ይጠቀሙ
ብርሃኑ የበዛ ፍላሽ ውበትዎን እንደሚገባው አጉልቶ ለማውጣት አይጠቅምም፡፡ ገፅታዎን ውብ አድርጎ የሚያወጣውን ትክክለኛ ብርሃን ሊያገኙ ይገባል፡፡ ለስላሳና ያልጎላ የጠዋት ብርሃን ወይም ጥላ ያለው የአመሻሽ ብርሃን ለፎቶው የተመጠነ ድምቀት ስለሚሰጠው ምስሉ ላይ ተፅእኖው አይበረታም፡፡ ኪም ካርዳሽያን በቅርቡ ከሜይል ኦንላይን ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ እንደተናገረችው ፊትዎን ብርሃን እንዲያገኘው መስኮት ጋ ቆመው ሰልፊዎን ይነሱ፤ ወይም ደግሞ የጥላ ተፅእኖን ለመቀነስ ፎቶዎን ወደጥቁርና ነጭ መልክ መቀየር ይችላሉ፡፡
5. ያጥሩት
የኢንስቶግራምን ተአምራዊ ስራ ሞክረውታል? ተራ ፎቶን ወደ ውብ ፎቶነት መቀየር ይችላል፡፡ አማሮ የተሰኘውን የኢንስቶግራም ምስል ማጥሪያ በመጠቀም ምስላቸው የጨለመ ፎቶዎችን ብሩህ ማድረግ ይቻላል፡፡ ናሽቪል የተባለው የምስል ማጥሪያ ደግሞ ምስሎችን የድሮ መልክ በመስጠት ወደኋላ ዘመን ሊወስደን ይችላል፣ ውብ ክፈፎች ወይም ፈሬሞችን ለፎቶው መጨመር እና ከጀርባ ያሉ ነገሮችን ፍዝ ማድረግ ይቻላል፡፡
ይገርማል! በጣም ቀላል ነገር፡፡ ቀጥሎስ? በቅርብ ርቀት አጉልተው ለሚያነሷቸው ቀጣይ የራስዎ ፎቶዎች ልምምድዎን ከወዲሁ ይጀምሩ፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ