ምርጥ ሙሽራ በሰርጓ ዕለት ውበቷን የሚመሰክር ቆንጆ የሰውነት ቆዳ ያስፈልጋታል
አገር ምድሩ በበርካታ ሰርጎች ደምቆ በምናይበት በዚህ ሰሞን አንቺም ከፊትሽ ለሚጠብቅሽ ታላቅ ቀን ቀድመሽ የምትዘጋጂበት ጊዜ ነው፡፡ ያለምንም ማመንታት ተውበሽ መታየት እና ስሜቱንም ማጣጣም ይኖርብሻል፡፡
እውነታው እንዲህ ነው! የሰርግሽ ቀን ስለአንድ ልዩ ሰው ብቻ የምንነጋገርባት ዕለት ናት – ስለአንቺ – ስለሙሽሪት! ያቺ ቀን በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ፍላጎቶችሽ፣ ህልሞችሽ እና ምኞቶችሽ ሁሉ እውን እንዲሆኑልሽ በሙሉ ሃይላቸው እና ከልባቸው ተፍ ተፍ የሚሉባት ቀን ናት፡፡ ሁሉም ለአንቺ ደስታ ዘብ የሚቆሙባት ታላቅ ቀን! ከልጅነትሽ ጀምሮ ስታልሚያት የኖርሻት ቀን ናት፡፡ የሰርግሽ ቀን በዓለም ላይ አብልጠሽ ለምትወጂው ሰው ልብሽን ለመስጠት ቃል የምትገቢባት ወሳኝ ዕለት ናት፡፡ ለዓይኖች እና ለካሜራዎች የአትኩሮታቸው ዋነኛ ማዕከል ሆነሽ የምትውይበት የህይወትሽ ወሳኝ ምዕራፍ የሚጀምርባት ልዩ ቀን!
ታዲያ በሰርግሽ ቀን እንደምትፈልጊው ልዩና ውብ ሆነሽ ለመታየት የሚያስችልሽን መልክ፣ ስሜት እና መዓዛ ለመጎናፀፍ ምን ማድረግ ይኖርብሻል? ላክስ ለዚህ መልስ አለው፡፡ ቀኑን ሙሉ ደምቀሽ እንድትታይ እና በልዩ ቀንሽ ለቆዳሽ ልዩ ውበት እንዲሰጥ ተደርጎ የተመረተው LUX Soft Touch Beauty Bar የውበት ጥያቄሽ ትክክለኛ ምላሽ ነው፡፡
ለስላሳ ቆዳ፣ በተፈጥሮ ውብ
የጠራ መልክ እና ፍፁም ውበትን የሚያላብሰው LUX Soft Touch Beauty Bar ለልዩ ቀንሽ እጅግ ተስማሚ ምርጫ ነው፡፡ ጥራታቸውን ከጠበቁ ምርጥ የመዋቢያ ምርቶቻችን አንዱ የሆነው LUX Soft Touch ከፈረንሳይ ሮዝ አበባ፣ ከለስላሳ ወይነጠጅ አበባ እንዲሁም ከቀይ ፍሬ እና ከSilk Essence ምጥን ቅመማ የሚመነጭ ጣፋጭ መዓዛን እና ልዩ የሰውነት ልስላሴን ያላብስሻል፡፡ ፍላጎትሽን ያላሟሉ ደረቅ እና ምቾት የማይሰጡ ሳሙናዎችን ስትጠቀሚ የከረምሺባቸውን ቀናት ተሰናብቺ እና በየቀኑ፣ በተለይ ደግሞ የሰርግሽ ቀን በዓለም ገንነሽ የመታየትን አይነት ልዩ እና አስደሳች ስሜት ተቀበይው፡፡
ማራኪ መዓዛን የተመለከቱ ነጥቦች
ለላክስ ምስጋና ይግባውና ጣፋጭ መዓዛ ባላቸው የፈረንሳይ ፅጌርዳ አበቦች በተሰራ ሳሙና በመታጠብ በቀላሉ የማይረሳ ልዩ ስሜትን መላበስ ይቻላል፡፡ ከአበባ እርሻ በትኩሱ የተለቀሙ ፅጌርዳ አበባዎች በዙሪያሽ ሲነሰነሱልሽ የሚሰማሽን አይነት ልዩ ምቾት እና ደስታ አጣጥመሽ ወዲያውም በፍቅረኛሽ ዘንድ ልዩ መለያሽ የሚሆን እና ከለስላሳ ገላሽ ላይ የሚቀር ድንቅ መዓዛ ለመላበስ ተዘጋጂ፡፡ በእርግጠኝነት የውበትሽን ብልጭታ አቀጣጥሎ ከፍቅረኛሽ ጋር ወዳለሽ ጣፋጭ የፍቅር ህይወት የሚመልስሽ ልዩ መዓዛ ነው፡፡ LUX Soft Touch Beauty Bar ከእያንዳንዱ የገላ ዕጥበት በኋላ በጣፋጭነቱ ፍፁም ማራኪ የሆነ መዓዛን ገላ ላይ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በሰርግሽ ዕለት በራስ የመተማመን ስሜትሽን እና የሴትነት ውበትሽን አጉልቶ በማውጣት ትዝታው መቼም የማይጠፋ የሰርግ ቀን እና አስደሳች ስሜትን ትቶልሽ ያልፋል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ