ላክስ የደማቅ ቀሚሶች ምርጫ
ፋሽን አድናቂዎች ብዙዎቻችን ቁምሳጥናችን ውስጥ አንዲት የምታምር አጭር ጥቁር ቀሚስ ትኖረናለች፡፡ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን አጭርና ደማቅ ቀሚስ ደግሞ ምን ያህል ውብ ሊሆን እንደሚችል መርሳት የለብዎትም፡፡
በዚህ ዓመት ቁምሳጥንዎን ለማድመቅ አጭርና ደማቅ ቀሚሶች ጥሩ ምርጫዎች ናቸው፡፡ ከምርጥ የመዋቢያ ምርቶች ጋር እንዲስማሙና ልዩ ውበትን እንዲያላብሱ ተደርገው በተለያዩ ቀለሞች ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ቀንዎን ብሩህ ለማድረግ የሚያስፈልግዎ አጭር፣ ደማቅ ቀሚስ ነው፡፡
ብሩሃማ አጭርና ልቅ ቀሚስ
ከሰውነት ቅርጽ ጋር የሚሄድ አጭርና ልቅ ቀሚስ ውበትና ግርማን ያላብሳል፡፡ ሆድዎን በአግባቡ ይሸፍናል፡፡ በተለይ የአፕል ቅርጽ መሳይ ሆድ ላላቸው ሴቶች ያን አካባቢ ክትት አርጎ ስለሚይዝላቸው ልቅ ቀሚስ ተመራጭ ነው፡፡ በተለይ ባለተረከዝ ጫማ ተጫምተው፣ ፀጉርዎን ወደኋላ ወይም መሃል ላይ ያዝ አድርገው ብሩሃማ ልቅ ቀሚስ ለብሰው ከወጡ የእግሮችዎን ቅርጽ ውበት አጉልተው ለማሳየት ይችላሉ፡፡ ዕድሉን እንዳገኙ ይሞክሩት፡፡
ሰውነት ላይ ልክክ የሚል ቀሚስ
ቀጭንና ውበቱን የጠበቁለት ሰውነት ካለዎት ብሩህ ቀለም ያለው ሰውነት ላይ ልክክ የሚል ቀሚስ ቢለብሱ የጥረትዎን ውጤት ውብ አድርጎ ያሳይልዎታል፡፡ እርስዎ ብቻ የመረጡት ቀሚስ ጥራት ያለውና አብዝቶ ሰውነትን የማያጋልጥ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ በሚያምር ቅርጽ ከተሰራ ባለተረከዝ ጫማ ጋር የሚስማማና ምሽት ላይ አምረው የሚወጡበት አለባበስ ነው፡፡
አንገቱ ወረድ ያለ ቀሚስ ቁመቱም ጉልበት አካባቢ ወይም ትንሽ ወረድ ያለ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምርጫዎችዎ እንደ ወይነ ጠጅ፣ ብርቱካናማ ወይም ቢጫ ያሉ ብዙ የማይዘወተሩ ቀለማት ከሆኑ ከነዚህ ቀለማት በአንዱ የተዘጋጀ ሰውነት ላይ ልክክ የሚል ቀሚስ ቢለብሱ ይመረጣል፡፡ ቀይ ቀለም ላይ ግን ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ገነው ከማይወጡ መዋቢያዎች ጋር ማስማማቱን ካላወቁበት ሰውነት ላይ ልክክ የሚል ቀይ ቀሚስ ባይለብሱ ይሻላል፡፡
እባክዎን ባለህትመት ቀሚስ!
በህትመትና በብሩህ ቀለማት አምሮ የተሰራ ቀሚስ ምርጫዎ ነው? የኛ ምርጫችን ነው! ውብ የህትመት ጥበብ ያረፈባቸውን በተለይም አሁን አሁን በተወሰኑ ቀለማት ፍርርቅ ወይም በአስደሳች አበቦች ህትመት ደምቀው የምናያቸውን ውብ ቀሚሶች እንወዳቸዋለን፡፡
ሞቃት ቀለማት
ሞቃት ብርቱካናማ በ2015 ልዩ ትኩረት ያገኘ ቀለም ሆኗል፡፡ ከፍዝ ሰማያዊ እስከ ደማቅ አረንጓዴ፣ ከደማቅ ሰማያዊ እስከ ብርቱካናማ ያሉ በጠቅላላው ፈካ ያሉ ቀለማትም እንደዚሁ ተወዳጅ ሆነዋል፡፡ በጣም ያልደመቁ ቀለማትን ከፈለጉ እንደመንደሪን፣ ሎሚ፣ ግራጫ እና ቀይ ብርቱካናማ አይነት ዝም ያሉ ቀለማትን ይምረጡ፡፡ ወይስ ደማቅ ቀለማት በጠቅላላ አይመቹዎትም? እንደዚያ ከሆነ ወርቃማና ብርማ ቀሚሶችን ቢለብሱ ልዩ መስህብን ይፈጥሩልዎታል፡፡ ጥቁር እና ነጭ ቀለማት ደግሞ ሁልጊዜም ፋሽን ናቸው፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ