ለጤናማ ቆዳ የሚበጁ 4 ጥቆማዎች
ቆዳን ከፀሐይ መጠበቅ እና በጥንቃቄ ማፅዳትን ጨምሮ ለሰውነት ቆዳ የሚደረግ ትክክለኛ እንክብካቤ ቆዳዎን ጤናማ ከማድረጉም በላይ ለመጪዎቹ በርካታ አመታት አንፀባራቂ ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ ይችላል፡፡ ለቆዳዎ ጥልቅ እንክብካቤ ለማድረግ ጊዜው የለኝም ብለው ቢያስቡ እንኳን መሰረታዊ የቆዳ እንክብካቤ በማድረግ ብቻ ምቾትዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ ትክክለኛ የቆዳ እንክብካቤ እና ጤናማ አኗኗር የተፈጥሮ እርጅናን ፍጥነት መግታት እና ቆዳ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ ችግሮችን መከላከል ያስችላል፡፡ ዋዛ ፈዛዛ በሌላቸው በሚከተሉት ጥቆማዎች ይጀምሩ፡፡
1) ቆዳዎን ከፀሐይ ብርሃን ጥቃት ይከላከሉት
ክረምቱ ገብቷል፡፡ ሆኖም እንደሌሎች ሀገራት የእኛ ሀገር ክረምት በሞቃታማ ቀናት የተሞላ እና ፀሐይ ለመሞቅ የምንተጋበት ወቅት አይደለም፡፡ ይልቁንም ማለቂያ የሌለው የሚመስል ርጥበታማ እና ዝናባማ ወቅት ነው፡፡ ነገር ግን እንዳይታለሉ፤ ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ ብቻ ቆዳዎ ከአደገኛ የፀሐይ ብርሃን ጥቃት ነፃ ነው ማለት አይደለም – አደገኛዎቹ የፀሐይ ጨረሮች በሃይል በሚወርደው ዝናብ እያንዳንዱ ጠብታ ውስጥ ሰርገው መግባት የሚችሉ ናቸው፡፡ ለማንኛውም ጊዜ የሚያገለግሉ የፀሐይ መከላከያ ቅባቶችን በየቀኑ መጠቀምን አይርሱ፡፡ ፀሐይ መከላከል አቅም ልኬቱንም ቢያንስ 30 ያድርጉት (SPF 30)፡፡ ምርጥ የሚባለው የመከላከል ርምጃ በራሱ ቀድሞ ርምጃ መውሰድን ያካትታል፡፡ በመሆኑም አስቀድመው ተግባራዊ ያደረጉት ጥሩ እንክብካቤ የተፈጥሮ እርጅናን ፍጥነት በመግታት እና ቆዳ ላይ ከሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮች በመጠበቅ የሰውነትዎን ቆዳ ለመጪዎቹ አመታት ጤናማ እና አንፀባራቂ ሆኖ እንዲቆይ ያደርግልዎታል፡፡
2) ቆዳዎን በጥንቃቄ ይንከባከቡት
በየቀኑ ቆዳን ማፅዳት እና መላጨት ቆዳዎን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ ጥንቃቄ ያድርጉ፡
- ሰውነትዎን ሲታጠቡ የሚቆዩበትን ጊዜ ውስን ያድርጉት፡፡ በጣም ሞቃት ውሃ እና ረጅም ጊዜ የሚወስድ ገላ መታጠብ ወይም ሻወር የቆዳዎን የተፈጥሮ ቅባት ጠራርጎ የመውሰድ አቅም አላቸው፡፡ የገላ እጥበት ወይም የሻወር ቆይታዎን ገደብ ያብጁለት፡፡ በተጨማሪም ከሙቅ ውሃ ይልቅ ለብ ያለ ውሃ ይጠቀሙ፡፡
- ጠንካራ ሳሙናዎችን አይጠቀሙ፡፡ ጠንካራ ሳሙና እና መሰል መታጠቢያዎች ከሰውነትዎ ላይ የተፈጥሮ ቅባትዎን ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ለሰውነትዎ ቀለል የሚሉዎትን እንደ Dove’s Beauty Bar ያሉትን ለስለሳ ሳሙናዎች ይጠቀሙ፡፡
- ቆዳዎን በጥንቃቄ ይላጩ፡፡ ቆዳዎን ከጉዳት ለመጠበቅ እና ለማለስለስ ከመላጨትዎ በፊት የመላጫ ክሬም፣ ሎሽን ወይም ጄል ይጠቀሙ፡፡ ጥርት አርጎ ለመላጨት ንፁህ እና የሰላ ምላጭ ይጠቀሙ፡፡ የፀጉሩን አስተዳደግ አቅጣጫ በመከተል ይላጩ ፡፡ በሌላ አነጋገር ሲላጩ ፀጉሩ በሚያድግበት አቅጣጫ ተቃራኒ አይላጩ፡፡
- ያደራርቁ፡፡ ታጥበው ሲጨርሱ ቆዳዎ ላይ ርጥበት እንዳይቀር በርጋታ ገላዎን በፎጣ ያደራርቁት
- • የቆዳዎን ርጥበት ይጠብቁ፡፡ ለቆዳዎ አይነት የሚስማማ ርጥበት መጠበቂያ ቅባት ይጠቀሙ፡፡ የቆዳ ድርቀት ችግር ካስቸገረዎ በሶስት ሳምንት ውስጥ ደረቅ የሰውነት ቆዳን ለመታደግ ተብሎ በልዩ መንገድ የተዘጋጀውን Vaseline’s Dry Skin Repair Lotion ለምን አይሞክሩትም!
3) ጤናማ አመጋገብ ይኑርዎት
ጤናማ አመጋገብ የምርጥ አቋም እና ስሜት ባለቤት እንዲሆኑ ይረዳዎታል፡፡ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን በብዛት ይመገቡ፡፡ በአመጋገብ እና በብጉር ማውጣት መካከል ያለው ግንኙነት ግልፅ ባይሆንም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ እና የቅባት መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ እንዲሁም በምግብ ፕሮሰሲንግ የተጣራ ካርቦሃይድሬት እንዲኖራቸው የተደረጉ ምግቦች ቆዳ ለጋነቱን ጠብቆ እንዲዘልቅ ያግዛሉ፡፡
4) ውጥረትን ይቆጣጠሩት
ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ውጥረት ቆዳዎን ለጉዳት ተጋላጭ ሊያደርገው ይችላል፡፡ በተጨማሪም የማዲያት መውጣት እና ሌሎች የቆዳ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ጤናማ ቆዳ እና አእምሯዊ መረጋጋት ይኖርዎ ዘንድ ውጥረትን የመቆጣጠሪያ ርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡ ለጥድፊያዎ ምክንያታዊ የሆነ ገደብ ያብጁለት፣ የሚሰሯቸውን ነገሮች ዝርዝር በልክ አድርገው የሚወዱትን ነገር ለማድረግም ጊዜ ይኑርዎት፡፡ እነዚህ ርምጃዎች የሚያመጡት በጎ ውጤት ከጠበቁት በላይ ሆኖ ሊያስደንቅዎ ይችላል፡፡
በቅርብ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶች
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by libe
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by alemugetahun
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by Risky
06 Jan 2015 @ 12:28 pm by belay
06 Jan 2015 @ 12:35 pm by መቅደላዊት ታከለ